Accounting and Auditing, Accounting System Design
ዑመማፍ የአረጋውያን እና ሕጻናት መርጃ ድርጅት የ2018 የበጀት ዓመት የፋይናንስ የሥራ ከንውን በቻርተር የተመሰከረለት የሂሳብ አዋቂ እና የተፈቀደለት የውጭ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል
Description
የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
ናዝሬት አዳማ የሚገኘው ዑመማፍ የአረጋውያን እና ሕጻናት መርጃ ድርጅት የ2018 የበጀት ዓመት የፋይናንስ የሥራ ከንውን በቻርተር የተመሰከረለት የሂሳብ አዋቂ እና የተፈቀደለት የውጭ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል፤
ስለሆነም ከዚህ በታች ተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ኦዲተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ሰነዳችሁን በታሸገ ፖስታ በማድረግ እና የድርጅቱን ማህተም በመምታት በአካል በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት በኋላ የሚመጡ ተወዳዳሪዎች በድርጅቱ ተቀባይነት እንደሌላቸው እናሳውቃለን፡፡
ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
1. የታደሰ የንግድ የስራ ፍቃድ
2. የሙያ ማረጋገጫ ፍቃድ
3. TIN (የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር)
4. Vat/TOT ሰርተፍኬት
5. ስራውን ሰርቶ ለማቅረብ የሚፈጅበት የጊዜ ገደብ እና
6. የገንዘብ መጠን በግልጽ መታየት (መቀመጥ) አለበት፡፡
አድራሻ፡- በኪዳነምህረት ቤ/ክርስቲያን በኮብልስቶኑ ገባ ብሎ ፖሊስ ጣቢያው ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡ 0927 326 543 / 0919 649 295
ዑመማፍ የአረጋውያን እና ሕጻናት መርጃ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-09-19
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች
- Bid opening: 2026-09-19 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Region: Oromia
- Publishing entity: Umemaf Elderly & Children Charity Organization
- Published on: Addis Zemen (Sep 09, 2026)
- Posted at: 2026-09-09T09:19:50.000Z
- Source: 2merkato