Vehicle

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት (የአውቶቡስ የኪራይ) አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል

Description

የአውቶቡስ የኪራይ አገልግሎት
ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ NEBE/NCB/03/2019

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ተኛው ቀሪና ድጋሚ ምርጫ የድጋሚ ምርጫ ለሚያካሒድባቸው የምርጫ ክልሎች አገልግሎት የሚውሉ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት (የአውቶቡስ የኪራይ) አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል።

1- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 (ብር ሁለት መቶ) በመክፈል ከቦርዱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 107 የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

2- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3- ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ክሊራንስ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ድረገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቦርዱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

5- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል።

6- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያነት ብር 100,000.00 (ብር አንድ መቶ ሺህ ብቻ) በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

7- ተጫራቾች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ ቦርዱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

8- ጨረታው መስከረም 11 ቀን 2019 ከሰዓት በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦርዱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

9- በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።

10- ቦርዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚንጎ ገባ ብሎ ባለው ዋ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻችን፡- ቦሌ ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡-+251 11 515 3468

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-21
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-09-21 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: National Election Board of Ethiopia
  • Buyer address: ቦሌ ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ
  • Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 10, 2026)
  • Posted at: 2026-09-10T07:22:16.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders