Accounting and Auditing, Accounting System Design
ንቁ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር (Niqu SACCOS) ለተከታታይ 3 አመት በየ3(ሶስት) ወሩ የበጀት ዓመታት የማኅበሩን ሂሳብ ኦዲት እንዲያደርጉ ይጋብዛል
Description
የፐብሊክ ኦዲተር የሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
ንቁ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር (Niqu SACCOS) የአባትን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ቀልጣፋ የብድርና የቁጠባ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ሲሆን፣ ፍላጎት ያላቸውን የፐብሊክ ኦዲት ድርጅቶች ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 3 አመት በየ3(ሶስት) ወሩ የበጀት ዓመታት የማኅበሩን ሂሳብ ኦዲት እንዲያደርጉ ይጋብዛል።
በመሆኑም በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የፐብሊክ ኦዲተር ፍቃድ የተሰጣቸው ተቋማት ብቻ
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የቫት ምዝገባና የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የታደሰ የምዝገባ ፈቃድ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል ተቋም!
- በሥራው ላይ በተለይም የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት (SACCOS) ኦዲት በማድረግ በቂ ልምድ ያለው
- የአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት የተከተለ ሂሳብ ኦዲት ያደረገና ልምድ ማቅረብ የሚችል!
- አግባብነት ያለው የኅብረት ሥራ ማኅበራት አዋጅና መመሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ የኦዲት ተቋም
- የሚቀርበው የጨረታ ዋጋ ከ2019-2021 ዓ.ም ድረስ ያለውን የሶስቱንም ዓመት (በየሶስት ወሩ የሚሰራውን ጨምሮ) ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
ንቁ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር (Niqu SACCOS) ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በዋናው መስሪያ ቤታችን በአካል በመቅረብ የሚሰሩበትን ዝርዝር ማብራሪያውንና ዋጋ (Technical and Financial Proposal) ከአስፈላጊ ሰነዶች ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን TOR እና የጨረታ ሰነድ በተጠቀሱት ቀናት ዋናው ቢሮ በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ንቁ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር (Niqu SACCOS)
ዋና አድራሻ፡- ንቁ አባዶ ቅርንጫፍ። የካ አባዶ ንደራ፣ ባጫ ሞል፣ 3ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር፡- 09 73 77 47 44 / 09 56 50 50 99 / 09 56 50 50 61
ኢሜል፡- [email protected] በንቃት ለሚተጉ እጆች
Tender details
- Deadline: 2026-09-18
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ
- Bid opening: 2026-09-18 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ንቁ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር (Niqu SACCOS)
- Published on: Reporter (Sep 09, 2026)
- Posted at: 2026-09-10T08:35:26.000Z
- Source: 2merkato