Building Construction
ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት በክረምት በጎ አድራጎት የመዋዕለ ሕጻናት መማሪያ ግንባታ፣ የአውቶቢስ ማጠቢያ ማሽን (Automatic Bus Washing System and Under Carriage Washer (Yeka, Akaki, Gullele and Jemo Sites) ግንባታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 004/2019 ዓ.ም
ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ግንባታ ስራ መሳተፍ የሚፈልጉ መስፈርቱን የሚያሟሉ ለሎት 1፣ ደረጃ 5 እና ለሎት 2፣ ደረጃ አንድ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1፣ በክረምት በጎ አድራጎት የመዋዕለ ሕጻናት መማሪያ ግንባታ ፤
- ሎት 2፣ የአውቶቢስ ማጠቢያ ማሽን (Automatic Bus Washing System and Under Carriage Washer (Yeka, Akaki, Gullele and Jemo Sites) ግንባታ ስራ፤
1. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር የስራ ቀናት ከሎት 1 እስከ ሎት 2 ለእያንዳንዱ ሎት 1000 በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 በአካል በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
2. ከሎት 1 እስከ ሎት 2 ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ ምዝገባና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤የብቃት ማረጋገጫ እና የአቅራቢዎች የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ፣ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) ያለቸው፤ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ከሎት 1 እስከ ሎት 2 ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የሚያቀርቡትን የጨረታ ሠነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ዋና እና ኮፒ በሁለት ፖስታ በማዘጋጀትና በኤንቨሎፕ በማሸግ፣ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት፣ ኃላፊነት በተሰጠው አካል ተፈርሞበት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 2% ሲፒኦ /Bid Bond) ወይም በባንክ የተመሰከረለት በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኃላ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል።
6 .አገልግሎታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሜክሲኮ ወደ ልደታ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ -011-5-50- 45-64
ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት
Tender details
- Deadline: 2026-09-26
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኃላ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-26 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኃላ 8፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Public Service Transport Service
- Bid bond: 2% ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 1000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Sep 12, 2026)
- Posted at: 2026-09-12T09:51:33.000Z
- Source: 2merkato