Event Organizing and Planning
አማራ ባንክ አ.ማ. የሁነት ዝግጅት አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የሁነት አገልግሎት ግዥ
የጨረታ ቁጥር፡- አባ/ግፋማመ/ሀግጨ/037/2026
(1) አማራ ባንክ አ.ማ በ2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ጃንሜዳ ለሚያካሄደው የባለአክስዮኖች ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሁነት ዝግጅት አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የአገልግሎት ዓይነት
|
ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት |
ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ስዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ
|
|
1 |
የሁነት ዝግጅት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት (Event Organizing Service)
|
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም. እስከ 8፡00
|
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
|
300,000.00
|
(2) ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከለገሃር ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በሚወስደው መንገድ መብራቱን እንደተሻገሩ የአመልድ ህንፃ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ግዥና ፋሲሊቲዎች አስተዳደር መምሪያ 20ኛ ፎቅ ላይ ከመስከረም 03 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ) የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
(3) ተጫራቾች ከጨረታው በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ከላይ በተገለፀው መሠረት ከጨረታው መክፈቻ ቀን ጀምሮ ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲፒኦ ወይም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሚሰጥ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአማራ ባንክ አ.ማ. ስም አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
(4) ተጫራቾች የሙያ ፈቃድ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
(5) ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት መሠረት ማስገባት አለባቸው። ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
(6) የጨረታው ሰነድ አማራ ባንክ አ.ማ. 20ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት መግባት ይኖርበታል።
(7) ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት አማራ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ግዥና ፋሊቲስ መምሪያ 20ኛ ፎቅ ይከፈታል።
(8) ከላይ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች አለማሟላት ከጨረታው ውጭ (ውድቅ) ያስደርጋል።
(9) ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 558 2905 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
(10) ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Amhara Bank S.C.
Beyond Financing
Tender details
- Deadline: 2026-09-22
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-09-22 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Amhara Bank S.C.
- Bid bond: 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Reporter (Sep 13, 2026)
- Posted at: 2026-09-14T09:08:18.000Z
- Source: 2merkato