House and Building Foreclosure
ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ. የመኖሪያ ቤት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የሐራጅ ማስታወቂያ
ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉብት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
በጨረታ የቀረበው ንብረት ዓይነት |
አበዳሪው ቅርንጫፍ
|
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ
|
የጨረታዉ ቀን እና ሰዓት
|
ጨረታው የወጣው
|
||
|
ከተማ፣ ክ/ከ ወረዳ ቀበሌ |
የባለቤትነት መረጋገጫ ቁጥር |
የቦታ ስፋት በካ.ሜ ሄ/ክ |
||||||||
|
1 |
አፋን ኮፊ ጀነራል ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር |
ወ/ሮ ሽታዬ አያሌው ወጋየው |
የመኖሪያ ቤት G+2
|
ባቦ |
ሸገር ከተማ፣መልካ ኖኖ ክ/ከተማ ወረዳ ቤሮ፣ዲያስፖራ ሰፈር ቦሪያድ ት/ቤት አካባቢ |
Bur/2845/98
|
250
|
21,191,529.04
|
በ03/02/2019 ዓ.ም ከ3፡00-4፡00 በዋና መ/ቤት
|
ለመጀመሪያ ጊዜ
|
|
2 |
ሳንተን ጀነራል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
እነ አብረሃም አሰፋ ተሰማ |
የመኖሪያ ቤት |
ለም ሆቴል
|
በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ለገሀር የሚወስድ መሸዋለኪያ መንገድ ላይ፣ |
AAOOOO 40901221
|
513 ካሜ
|
18,500,000.00
|
በ03/02/201ዓ.ም ከ4፡30-5፡30 ሰዓት በዋና መስሪያ ቤት |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
1.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲፒኦ በኦሮሚያ ባንክ ስም አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል።
2.ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ቦሌ መንገድ ኦሎምፒያ አካባቢ ኦሜዳድ ሆቴል ጎን የኦሮሚያ ባንክ ህግ አገልግሎት ቢሮ የሚገኝበት ናትሩት ሀውስ (ህንፃ) 9ኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ የጨረታ አዳራሽ ውስጥ፣ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል። ባለ ዕዳዎቹ ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል።
3.የተጨራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝግያ ስዓት 5 ደቅቃ በፊት ይጠናቀቃል። የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ አስኪለይ ደረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል። በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ ህግ አገልግሎት ሊደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
4.ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል።
5.በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል::
6.ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የስም ማዘወሪያ እና ማናቸዉም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀው ክፍያ ይከፍላል።ንብረቱ በገገርው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
7.ውዝፍ የሊዝ ክፍያን በተመለከተ ከእዳ ተመላሽ ብር ካለ ከተመላሽ ብር ላይ የሚከፈል ሲሆን ተመላሽ ብር ከሌለ ግን የንብረቱ ጨረታ አሸናፊ ውዝፍ የሊዝ ክፍያን ሙሉ በሙሉ የሚከፍል ይሆናል።
8.ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ይችላሉ።
9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 1372 ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት፣ ለተራ ቁ.1 በ 0113/71-30-72/65/74 /0118-96-02-71 ኦሮሚያ ባንክ ባቦ ቅርንጫፍ ለተራ ቁ.2 በ011-6-59-14-21/08-82 ኦሮሚያ ባንክ ለም ሆቴል ቅርንጫፍ ደውለው መጠየቅ ይቻላል። ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
10. ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-10-13
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታው ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-10-13 12:00
- Bid opening (note): የጨረታው ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published on: Reporter (Sep 13, 2026)
- Posted at: 2026-09-14T11:33:45.000Z
- Source: 2merkato