Food Items and Drinks
የድሬዳዋ ሁሉ አቀፍ ማረሚያና ማረፊያ ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት አመት ለህግ ታራሚዎች አገልገሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግለፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የድሬ ዳዋ ሁሉ አቀፍ ማረሚያና ማረፊያ ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት አመት ለህግታራሚዎች ምግብ አገልገሎት የሚውሉ
- የተለያዩ እህሎች፣ ጥራ ጥሬዎች፣ ማጣፈጫዎች፣ ለጥገናና የስልጠና ግብዓት፣
- ለብረታ ብረትና እንጨት ስራ፣ የፅህፈት መሣሪያ፣ ለፅዳትና ለካፊል ቀሚ ዕቃዎች፣
- ለኤሌክትሪክና ለአውቶማካኒከ ሥልጠና፣ ለልብስ ስፌት ሥራ ስልጠናና
- ለደንብ ልብስ አገልግሎት የሚውሉ ጨርቃ ጨርቅና ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
ከላይ የተገለፁትን ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማሩትን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የሚፈለግባቸውን የመንግስት ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ መደረጉን የሚያረጋግጡ መረጃዎች የዕቃ(የአጋልግሎት) አቅራቢዎች ምዝገባ ስለመታቀፋችው ከንግድ ሚንስቴር የተሰጣቹን የምዝገባ ምስክር ወረቀት ወይም ከግዝ ኤጄንሲ በተለቀቀ የመረጃ መረብ ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኙ እንዲሁም የሀጋር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት እና ሌሎች ህጋዊ ማስረጃዎችን ስዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ስለሆነም፡-
1. ተጫረቾች የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት የቴክኒክና የዋጋው ሰነድ በአንድ ኤንቨሎፕ በማድረግና በማሸግ በግልፅ በፖስታው ላይ በመፃፍና በመፈረም ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በታሸገ ፖስታ ማስገባት አለባቸው።
2. ተጫራቾች ይህ ማስተወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15(አስራ አምስት) ቀን በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት በድሬ ዳዋ ማ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 311 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከባንክ በተረጋገጠ cpo ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ።
4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በተመለከተ እንደሁም ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን በጨረታ ሰነድ ውስጥ ያገኙታል።
5. ተጫራቾች ሰነዶችን ለማስገባት ስመጡ ለሚጨረቱባቸው የዕቃዎች ናሙና አብረው ማቅረብ አለባቸው።
6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኚም ባይገኙም የቴክንካልና የፋይናንሻል የጨረታ ሰነዱ በመ/ቤታችን በተበለው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በካፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
የድሬዳዋ ሁሉ አቀፍ ማረሚያና ማረፊያ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-29
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አስራ አምስት) ቀን
- Bid opening: 2026-09-29 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: Dire-Dawa Correctional Facility
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 15, 2026)
- Posted at: 2026-09-15T08:14:50.000Z
- Source: 2merkato