Consumable Goods

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የምግብ ሸቀጣሸቀጥ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዥዎች ለመፈጸም አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. የምግብ ሸቀጣሸቀጥ

ስለዚህም

  • በዘርፉ ሀጋዊ ለ2019ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈለና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  • የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃና የአገልግሎት አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገበና ለዚህም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  • የግብር መክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢነት ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  • በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
  • ታክስ ክሪላንስ የ2019ዓ.ም ማቅረብ የሚችል
  • ተጫራቾች ጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት የሚችል
  • ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ከጨረታ ሰነዱ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 21 ተከታታይ ቀናት ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመቅረብ የሚወዳደሩትን ዋጋ በመሙላት እና ከላይ የተጠቀሱትን ህጋዊ ሰነዶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 4:00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ በዛው እለት ከጠዋቱ በ4፡ 30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ግን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡-

1. ቢሮው ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 02511128435 መደወል ይችላሉ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-07
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 4:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-07 10:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Dire Dawa Adminstration Education Bureau
  • Buyer address: Dire Dawa Administration Education office Dire Dawa Ethiopia
  • Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 400 (አራት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 16, 2026)
  • Posted at: 2026-09-16T09:05:46.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders