House and Building Sale
የቦታው ስፋት 692 ካ.ሜ. ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍርድ ባለመብት እነ ሀብቴ ዓለሙ እና በፍርድ ባለእዳ እነ ምናሴ ዓለሙ መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 278167 በ20/8/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ በአዲስ አበባ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 1039 የሆነውና በካርታ ቁጥር አ17/35/0800/02 በፍ/ባለእዳ አውራሽ አቶ ዘላለም መንግሥቱ ጓለ ስም የተመዘገበ የቦታ ስፋት በይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ላይ እንደሰፈረው 692 ካ.ሜ ይዞታው ከ4ኪሎ ሽሮሜዳ ጉለሌ እፅዋት ማእከል በተሠራው የኮሪዶር ልማት ፕላን ውስጥ ያለ አዋሳኞቹ በምስራቅ ቤተከህነት፣ በምዕራብ አቶ ታደሰ በደቡብ መንገድ በሰሜን ግርማ ወሰኔ የቤቱ የሽያጭ ዋጋ መነሻ ግምት ብር 29,696,566 (ሃያ ዘጠኝ ሚሊዮን ስድስት መቶ ዘጠና ስድስት ሺ አምስት መቶ ስልሳ ስድስት ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/ አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-19
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-10-19 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Sep 17, 2026)
- Posted at: 2026-09-17T08:29:06.000Z
- Source: 2merkato