House and Building Foreclosure
የይዞታው ስፋት 177 ካ.ሜ. ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍርድ ባለመብት አቶ ዘሪሁን እንደሻው እና በፍርድ ባለእዳ ዝናሽ እንደሻው መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 324943 በ10/03/2018ዓ.ም በኮ/መ/ቁ.330359 በ20/5/2018 ዓ.ም እና በመ/ቁ 324943 በ13/05/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት በልደታ ክ/ከተማ በቀድሞ ወረዳ 08 በአሁኑ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 187 የካርታ ቁጥር 002085 የሆነው ቤት እና ይዞታ የተመዘገበው በአቶ እንደሻው ተክለሥላሴ የይዞታው ስፋት 177ካ.ሜ የቤቱ የሽያጭ ዋጋ መነሻ ግምት ብር 9,080,121 (ዘጠኝ ሚሊዮን ሰማንያ ሺህ አንድ መቶ ሃያ አንድ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.330359 በ27/2/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት 1/4ኛ 2,270,030.25 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰባ ሺህ ሠላሳ ብር ከ25/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረበ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ cPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም c.PO አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-20
- Bid closing time: 11:30
- Bid opening: 2026-10-20 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
- Posted at: 2026-09-18T08:29:04.000Z
- Source: 2merkato