Water Pipes and Fittings
የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል
ጨረታ ቁጥር (1) ለእንጨትና ብረታ ብረት ለትምህርትና ስልጠና ስራዎች አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ ግብዓቶች፣ የቧንቧ ዕቃዎች፤ የተለያዩ ለትምህርት እና ለንባብ አገልግሎት የሚውሉ መጽሐፎች
ጨረታ ቁጥር (2) የሲቪል ሰራተኞች፤ የስፖረተኞች የሥራ ልብስና ጫማዎች እንዲሁም በህግ ታራሚዎች አግልግሎት የሚውል ዩኒፎርም ብትን ጨርቅ ፤ የእንስሳት መኖ ግብዓቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
1. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ፤ በሥራው መስክ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በዕቃ ግዢና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበት የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ እና መለያ ቁጥር (Tin Number) ተመዝጋቢ የሆኑና የተሟላ ማስረጃ በ4 ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን አንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመሰስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000007971188 አ/አ ማረ/ቤት እደ-ጥበባት ማዕከል በሚል ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ግዥ ከንውን ቡድን 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ዶችላሉ። ማ/ቤቱ የሚገዛቸውን ዕቃዎች ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተዘርዝሮ ቀርቧል።
3. ተጫራቾች ከላይ በጨረታ ቁጥር 1-2 ለተጠቀሱት ጨረታዎች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚመለስ ለእያንዳንዳቸው ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው “ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች አንዱ በሌላው ተጫራች ሰነድ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።
5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ሳይ ናሙና እንዲያቀርብ የተጠየቀባቸው ናሙናውን በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነድ መግዛትና የመተዳደሪያ ሃሳባቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ አሽገው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፣
6. ተጫራቾች የጨረታ ቁጥር 1 መስከረም 26/2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዕለቱ በ4፡15 ሰዓት በማረ/ቤቱ በግዥ ክንውን ቢሮ ይከፈታል።
7. የጨረታ ቁጥር 2 መስከረም 27/2019ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት ይችላሉ:: በዕለቱ በ4፡15 ሰዓት በማ/ቤቱ አደራሽ ይከፈታል።
8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል /ገላን በሚገኘው ዕቃ ግ/ቤት አምጥተው ያስረክባሉ።
9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ሳይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
10. ማረሚያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ተጫራቾች ፕሮፎርማቸው ላይ ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ጎላ ብሎ የሚነበብ ፅሑፍ መሆን ይገባዋል፤ ስርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ተቀባይነት የለውም:: በአሃዝና በፊደል መፃፍ ይጠበቅባቸዋል።
አድራሻ፦ የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል
ገላን
የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል
Tender details
- Deadline: 2026-10-07
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-10-07 10:15
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: High Security Prison Center
- Buyer address: ቃሊቲ ክራውን ሆቴል ፊት ለፊት
- Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዳቸው
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
- Posted at: 2026-09-18T09:57:21.000Z
- Source: 2merkato