Construction Machinery

የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (OCC) የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን፣ ፕላንቶችን፣ ከባድ መኪኖችን እና አነስተኛ የመስክ መኪኖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ግልጽ ጨረታ ቁጥር NCB/OCC‐042/2026

የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (OCC) በ2019 ዓ.ም በኦሮሚያና በሌሎች ክልሎች ለሚያካሂደው ለመንገድ ሥራ ግንባታ፤ ለሕንጻ ሥራ ግንባታ፤ ለመስኖ ሥራ ግንባታ፤ ለውኃ ሥራ እና ለውኃ ቁፋሮ ሥራ ግንባታ እና ለክሬሸር ማምረቻ አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን፤ ፕላንቶችን፤ ከባድ መኪኖችን እና አነስተኛ የመስክ መኪኖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።

የሚፈለገው የመሳሪያ ዓይነት ዝርዝር ለተጫራቾች በሚሸጠው የጨረታ መመሪያ ሠነድ ውስጥ ተካቷል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያስባቸው መስፈርቶች፡

  1. ከሥራው ጋር አግባብነት ያለው እና የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፤ የሚፈለግባቸውን የመንግስት የግብር ግዴታ ስለመወጣቱ የሚያመለከት ጊዜው ያላለፈበት ማስረጃ (ታክስ ክሊራንስ) ከሚመለከታቸው አካላት ማቅረብ የሚችል፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) እና ከግዥና ንብረት አስወጋጅ ባለስልጣን ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ እና የተመዘገቡበትን የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤታችን አንደኛ ፎቅ ኮርፖሬት ግዥ ቡድን ከፍል መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ “CPO” ወይም በቅደመ ሁኔታዎች በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (unconditional & Irrevocable Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች፤ ፕነቶች እና ተሽከርካሪዎች ከአከባቢ ጥበቃ ደህንነት (Environment) ጋር የሚጣጣሙ መሆን አለባቸው። እንዲሁም ሠራተኞችን ልያጋጥሙ ከሚችሉ የሥራ ላይ አደጋዎች እና ደህንነት (OSH) ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ማሽነሪዎቸ አቋማቸው የተሟላ መሆን አለበት።
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የአገልግሎት ዓይነት ድርጅታችን ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ መስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ማለትም መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም 8:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በኮረፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
  6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዜደ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- አቃቂ ቃሊት ወረዳ 05 ከአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ማዕከል ፊት ለፊት OCC ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ኮርፖሬት ግዥ ቡድን ክፍል።

ስልክ ቁጥር፡-+251-0114-39-04-22/0114-39-13-07

ኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን(OCC)


Tender details

  • Deadline: 2026-10-08
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-10-08 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Oromia Construction Corporation (OCC)
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 19, 2026)
  • Posted at: 2026-09-19T08:04:10.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders