Printed Advertising Materials
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለሰራተኞች የመታወቂያ ባጅ ከነማንጠልጠያው ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ(በድጋሚ የወጣ)
CN/NCB/04/19
ድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለሰራተኞች የመታወቂያ ባጅ ከነማንጠልጠያው ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም ሰራተኞች የመታወቂያ ባጅ ከነማንጠልጠያው መስራት የሚችሉ ድርጅቶችን በሀገር ዓቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት የመሳሰሉትን የቴክኒክ ሰነዶች በተለየ የታሸገ ፖስታ እንዲሁም ፋይናንሻል ዶክመንት በተለየ ሁለተኛ የታሽገ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡ የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመከፈል ከሰኞ እስከ ዓርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) እና ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100000.00(መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 ጠዋት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ጠዋት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት
ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569992
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-10-01
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-01 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Commercial Nominees P.L.C.
- Buyer TIN: 0000958158
- Buyer address: ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 20, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T08:40:05.000Z
- Buyer website: https://commercialnominees.com/
- Source: 2merkato