Printed Advertising Materials
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ በ2019 ዓ.ም በተፈቀደ መደበኛ በጀት የሕትመት የግብዓት እቃዎች እና የስንዴ ዱቄት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Description
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር E/M/T/C/E NCB/02/2019
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ በ2019 ዓ.ም በተፈቀደ መደበኛ በጀት
- የሕትመት የግብዓት እቃዎች እና
- የስንዴ ዱቄት ግዥ
በዘርፉ ንግድ ፈቃድ አውጥተው ከተሰማሩ ሕጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
- በዘርፉ የወጣና ለዘመኑ የንግድ ሥራ ፈቃድ ኮፒ፣ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ኮፒ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ኮፒ ፣ በማንኛውም የመንግሥት ግዥ ጨረታ እንዲሳተፉ በሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የተሰጠ ድጋፍ ደብዳቤ ኮፒ ፈርመውና በድርጅታቸው ማህተም አረጋግጠው ዋናውን ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም፣ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 1% ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ ሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በእቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ስም አሠርተው ማቅረብ አለባቸው። በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ከ90 ቀን በታች መሆን የለበትም።
- ተጫራቾች በተ.ቁ 1 እና 2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ እንዲሁም የዋጋ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግና በማያሻማ ሁኔታ በጀርባው ላይ ኦርጅናልና ኮፒ በሚል ቃል በጽሑፍ በማመላከትና በድርጅታቸው ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው።
- ሁሉም (ሶስቱም) ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ ተጠቃለው ታሽገውና በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጠው መግባት አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስና አስተዳደር ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 06 የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነዳቸውን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታውም ታዛቢዎችና ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡01 ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ይከፈታል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-10-05
- Bid closing time: 10:01
- Bid closing (note): ይህ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡01 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-05 10:30
- Bid opening (note): ይህ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Gondar University Etege Mentwab Trade and Consulting Enterprise
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 20, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T09:25:34.000Z
- Source: 2merkato