Pharmaceutical Products
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ መድሀኒቶች፣ የንጽህና መጠበቂያዎች፣ ተጨማሪ የህጻናት ምግቦች እና የህከምና ግብዓት እቃዎችን በዘርፉ ንግድ ፈቃድ አውጥተው ከተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Pharmaceutical ProductsHealth Care, Medical IndustryCleaning and Janitorial Equipment and Service
Amhara
Description
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር E/M/T/C/E/NCB/01/2019
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ለእቴጌ ምንትዋብ ሞዴል መድሀኒት ቤት አገልግሎት የሚውል
- የተለያዩ መድሀኒቶች፣
- የንጽህና መጠበቂያዎች፣
- ተጨማሪ የህጻናት ምግቦች እና
- የህከምና ግብዓት እቃዎችን
- በዘርፉ ንግድ ፈቃድ አውጥተው ከተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
- በዘርፉ የወጣና ለዘመነ የንግድ ስራ ፈቃድ ኮፒ፣ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ኮፒ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርትፊኬት ኮፒ፣ በማንኛውም የመንግስት ግዥ ጨረታ ሰርትፍኬት እንዲሳተፉ በሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የተሰጠ ድጋፍ ደብዳቤ ኮፒ ፈርመውና በድርጅታቸው ማህተም አረጋግጠው ዋናውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 1% ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚስጥ ሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በእቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ስም አሰርተው ማቅረብ ( አለባቸው፡፡ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ከ90 ቀን በታች መሆን የለበትም፡፡
- ተጫራቾች በተ.ቁ 1 እና 2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ እንዲሁም የዋጋ መወዳደርያ ስነዳቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግና በማያሻማ ሁኔታ በጀርባው ላይ ኦርጅናልና ኮፒ በሚል ቃል በጽሁፍ በማመላከትና በድርጅታቸው ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ሁሉም (ሶስቱም) ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ ተጠቃለው ታሽገውና በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጠው መግባት አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስና አስተዳደር ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 06 የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደርያ ሰነዳቸውን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታውም ታዛቢዎችና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት 4፡01 ታሽጎ በእለቱ 4፡30 እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ቢያንስ 90 ቀን ድረስ ጸንቶ መቆየት አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎችን ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋ ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ የታክስ ሁኔታ ያልተገለጸ ከሆነ የተሞላው ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ታክስና ወጭን አካቶ እንደተላከ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
- ተጫራቾች ወይም አቅራቢዎች ዋጋውን የሚሞሉት ከአከፋፋዮች ከገዙበት ዋጋ ላይ በተፈቀደላቸው የትርፍ ህዳግ መሰረት በፐርሰንት ዋጋ የሚሞሉ ይሆናል
- ተጫራቾች ዋጋውን ሲሞሉ ከአስመጭዎች የገዙበትን የዋጋ ዝርዝር ህጋዊ፣ ግልጽ፣ የሚነበብና የሚታይ መረጃ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ።
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ በቀጣይ የሁለት (2) ዓመታት በወቅቱ በሚኖረው የገበያ ሁኔታመድሀኒቶችን እና የህክምና ግብዓት እቃዎችን ለማቅረብ የኮንትራት ውል ስምምነት (contractual agreement) ለመውሰድ ፈቃደኛ መሆን እና ዋጋው ሲቀንስ አትራቢዎች ሊቀንሱ ዋጋው ሲጨምር ደግሞ ኢንተርፕራይዙ ሊጨምር የሚስማሙ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ ከተዘረዘሩት መድሀኒቶችና ህክምና ግብዓቶች አይነቶች ውስጥ ቢያንስ 25% በላይ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ኢንተርፕራይዙ አሁን ከጠቀሳቸው መድሀኒቶችና የህክምና ግብዓት እቃዎች በተጨማሪ በቀጣይ ለመግዛት ቢፈልግ አሸናፊ አቅራቢዎች አሁን ባቀረቡት መድሀኒቶችን፣ ህክምና ግብዓቶችን እና ተጨማሪ የህጻናት ምግቦችን ባሸነፉበት መስፈርት አሁን በዝርዝሩ ያልተጠቀሱትን ሌሎችንም ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆን ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ አቅራቢዎች የሚያቀርቧቸው መድሀኒቶችና የህክምና ግብዓቶች የመጠቀሚያ አገልግሎት ጊዜያቸው (expire date) ከአንድ ዓመት በላይ የቀረው መሆን አለበት፡፡
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0918777942 ወይም 0918053797 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-10-05
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-05 10:30
- Bid opening (note): ይህ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Gondar University Etege Mentwab Trade and Consulting Enterprise
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 20, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T10:12:35.000Z
- Source: 2merkato