Construction Machinery
ውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች የኪራይ የአገልግሎት ግዥ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ሃገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር WWC 02/2019
ውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት የኮርፖሬሽኑን ሥራ ለማፋጠን ለተለያዩ ለፐሮጀክቶች አገልግሎት የሚሆን
- የተለያዩ ማሽነሪዎችና
- ተሽከርካሪዎች የኪራይ የአገልግሎት ግዥ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ፤የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት የንግድ የምዝገባ ምስከር ወረቀት እና የንብረቱ ባለቤት ስለመሆኑ ማስረጃ ያላቸው መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባዉ ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ይሆናል።
- በዚህ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ 20 /ሃያ ተከታታይ ቀናት ውስጥ በመምጣት የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺ ብር/ በቀጥታ ከኮርፖሬሽናችን የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ሰነዱ የሚሸጥባቸው ቦታዎች ባህር ዳር ዋናው ቢሮ በአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እና ኮምቦልቻ ውኃ ሥራዎች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ይገኛል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመሣሪያ ብዛት መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ቀላል ተሽከርካሪ አምቡላንስ ፣ዳብል ጋቢና፣ ሲንግልጋቢና፣ ሚኒ ጋቢና፣ ሚኒባስ፣ አውቶሞቢል፣ ስቴሽንዋግንና ተመሳሳይ ለሆኑት /20 ሺህ ብር/፣ መለስተኛ የህዝብና የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች አይሱዙና አውቶብስ/ 25ሺህ ብር፣ ከባድ ተሽከርካሪ /ገልባጭ 120 ኩንታል በላይ የሚጭኑ የደረቅ እና የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ፣ ሚክሰር፣ ትራክተር፣ ከሬን/ 30 ሺህ ብር፣ ለቀላል ማሽነሪዎች ኮምፖከተር፣ ሎደር/ 35 ሺህ ብር እና ለከባድ ማሸነሪነዎች /ዶዘር፣ ኤክስካቫተር፣ ግሬደር፣ ሎቤድ/ 40 ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ /CPO/ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል [Unconditional Bank guarantee/ የባንክ ጋራንቲ በማሰራት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች የማወዳደሪያ ሠነዳቸው በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 20 ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤታችን ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 25 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 መሰናዶ ት/ቤት ጐን በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ህንጻ 3ኛ ፎቅ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 25 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉሉም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፉ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡ የጨረታው መክፈቻ እና መዝጊያ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ካሸነፉ በኮርፖሬሽኑ ስምምነት መሰረት የቅድመ ክፍያ ሊከፍል ይችላ።
- ተጫራቾች በጨረታው መመሪያ መሠረት የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማቅረብ አለባቸው ከጨረታው መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በአንድ ማሸን ወይም ተሽከርካሪ መወዳደር የሚችሉት አንድ ኘሮጀክት ብቻ ላይ ነው።
- ኮርፖሬሽን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።
የስልክ ቁጥር ባህር ዳር 058-222-1479 ወይም 058226-5203
አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት 011-443-2595
ኮምቦልቻ ምስራቅ አማራ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት 033-5510230 ወይም 033-5510848
ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-10-09
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-09 14:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Water Works Construction Enterprise
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 1000.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 20, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T11:33:33.000Z
- Source: 2merkato