Audio Visual, Photography and Filming Service and Equipment

አማራ ባንክ አ.ማ. የመድረክ፣ የሳውንድ ሲስተም፣ የስክሪን አቅርቦት፣ ቀጥታ ስርጭት እና ዶክመንቴሽን፤ (Stage Sound System, Screen, Live stream and documentation Service) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- አባ/ግፋማመ/ሀግጨ/039/2026

(1) አማራ ባንክ አ.ማ ህዳር 27 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ጃንሜዳ ለሚያካሄደው የባለአክስዮኖች ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ ለሚደረግ ሁነት ዝግጅት ግብዓት ሆነው የሚያገለግሉ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተጠቀሱትን የተለያዩ አገልግሎት እና አቅርቦቶችን በብቃት መፈፀም የሚችሉ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ሎት

የአገልግሎት ዓይነት

ጨረታው የሚዘጋበት ንና ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት

የጨረታ ማስከበሪያ

 

1

የመድረክ፣ የሳውንድ ሲስተም፣ የስክሪን አቅርቦት፣ ቀጥታ ስርጭት እና ዶክመንቴሽን፤ (Stage Sound System, Screen, Live stream and documentation Service)

መስከረም 20 ቀን 2019 ..እስከ 800 ዓት

 

መስከረም 20 ቀን 2019 .. ከቀኑ 830 ሰዓት

200,000.00

 

(2) ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከለገሃር ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በሚወስደው መንገድ መብራቱን እንደተሻገሩ የአመልድ ህንፃ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ግዥና ፋሲሊቲዎች አስተዳደር መምሪያ 20ኛ ወለል ላይ ከመስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ) የምድር ወለል ላይ የሚገኘው አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።

(3) ተጫራቾች ከጨረታው በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ከላይ በተገለፀው መሠረት ከጨረታው መክፈቻ ቀን ጀምሮ ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲፒኦ ወይም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሚሰጥ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአማራ ባንክ አ.ማ. ስም አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

(4) ተጫራቾች የሙያ ፈቃድ፣የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

(5) ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት መሠረት ማስገባት አለባቸው። ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

(6) የጨረታው ሰነድ አማራ ባንክ አ.ማ. 20ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት መግባት ይኖርበታል።

(7) ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት አማራ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ግዥና ፋሊቲስ መምሪያ 20ኛ ፎቅ ይከፈታል።

(8) ከላይ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች አለማሟላት ከጨረታው ውጭ (ውድቅ) ያስደርጋል።

(9) ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 558-2905 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

(10) ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አማራ ባንክ አ.ማ

ከባንክ ባሻገር!


Tender details

  • Deadline: 2026-09-30
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-09-30 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Amhara Bank S.C.
  • Bid bond: 200,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Reporter (Sep 20, 2026)
  • Posted at: 2026-09-21T13:22:21.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders