Building Construction
ፀደይ ባንክ አ.ማ. የተለያዩ ስራዎችን ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/001/2019
ፀደይ ባንክ አ.ማ. ከስር የተዘረዘሩትን ዕቃዎች/ስራዎች አገልግሎቶች ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ ማሰራት ይፈልጋል::
|
ሎት 1 |
የህንፃ ግንባታ እድሳት ስራ አዲስ ዘመን ፤ ወረታ እና አዴት ቅርንጫፎች BC/ GC -7 and above
|
|
ሎት 2 |
የህንፃ ግንባታ እድሳት ስራ ሞጣ ደንበጫ እና ቻግኒ ቅርንጫፎች BC/ GC -7 and above
|
|
ሎት 3 |
Consultancy Service (Category. -III and above) for Preparation of Detailed Design, Tender Documents, Cost Estimates/BOQ and Construction Supervision Consultancy Services of Tsedey Bank Branch Buildings at
|
ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት/ነጋዴ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን::
1. የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ # የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት # በጨረታ ለመካፈል/ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት/ ክሊራንስ ጊዜው ያላለፈበት:: ቴክኒካል ዶክመንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::
2. ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በሲፒኦ / CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ90 ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል:: ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አ.ማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም ::
3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ የሂሳብ ቁጥር 1201390000037 በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ::
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታው እስከሚዘጋበት መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታው በተዘጋበት ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
5, የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም::
6. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው የፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት ስልክ ቁጥር 0115581658
ፀደይ ባንክ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-10-06
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-06 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
- Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
- Bid bond: የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00
- Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Reporter (Sep 20, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T13:55:25.000Z
- Source: 2merkato