Vehicle
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2019
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግዥ ጨረታ።
- ሎት 1. የመኪና ኪራይ-20000/ሃያ ሺህ /ብር
- ሎት 2. ህትመት ስራ-20000/ሃያ ሺህ /ብር
- ሎት 3. እስቴሽነሪ እና የቢሮ እቃዎች-30000/ሰላሳ ሺህ/ ብር
- ሎት 4. የደንብ ልብስ እና ጫማ-50000/ሃምሳ ሺህ/ ብር
- ሎት 5. የመኪና ጥገና ጋራዥ -20000/ሃያ ሺህ/ ብር
- ሎት 6.የከተማ ውበት የሚያገለግሉ ግብዓትና የልማት እቃዎችና መሳሪያዎች-20000/ሃያ ሺህ/ ብር
- ሎት 7 የከባድ የመኪና ጎማዎች ከነከመነዳሪው-20000/ሃያ ሺህ/ ብር
1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ምዝገባ እና ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. በመንግስት የግዥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል Tin No ያላቸውና በገንዘቡና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ሠነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10/አስር/ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያና ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ ከላይ በተቀመጠው አግባብ በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ተከታታይ የሥራ ቀናት በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. ሰነድ የሚመልሱበት በ11ኛው ቀን የስራ ሰዓት ተመልሶ የስራ ቀን በ8፡30 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይከፈታል።
9. የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል እና ኮፒ ተሞልቶና ኦርጅናሉ ኮፒው ተለይቶ በፖስታው ላይ ተፅፎ መቅረብ ይኖርበታል።
10. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና የስፈለጋቸው ማቅረብና ሌሎችንም ዕቃዎች በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሠረት ዋጋቸውን በአግባቡ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
11. ናሙና ያልቀረበበት፣ የዘገየ፣ በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ እንዲሁም ከጨረታ ሠነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡በጨረታ ሠነድ ክፍል 4, 6 እና 9 የተቀመጡ ግዴታዎች ከሰነዱ ጋር ተሞልተው ያልቀረቡ ጨረታዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
12. አሸናፊ ተጫራቾች 10% የውል ማስረከቢያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
13. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈባቸው ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት መጋዘን ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
14. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ለገቢያ በሚቀርብበት ዕቃ/ምርት ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጀ ምርት/ዕቃ ከገቢያ ላይ ገዝተው ለሚወዳደሩት እያንዳንዱ ምርት ዕቃ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
15. ስርዝ ድልዝ መረጃዎች ተቀባይነት የላቸውም።
16. መ/ቤቱ ለግዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ በሚወሰደው መንገድ አዲሱ የክፍለ ከተማ ህንጻ ላይ 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302 የአራዳ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን ስልክ ቁጥር 0900 019 739 -የአራዳ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 14:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን የስራ ሰዓት ተመልሶ የስራ ቀን በ8፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-02 15:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን የስራ ሰዓት ተመልሶ የስራ ቀን በ9፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Arada Sub City Administration Design and Construction Work Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 21, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T07:05:39.000Z
- Source: 2merkato