Food and Beverage
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የትራንስፖርት አገልግሎት እና የቲማቲም ድልህ ለመጀመሪያ ዙር በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አሳዉጆ ህጋዊ ከሆኑ ነጋዴዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Description
ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዋ/ዩ/ዱ/ካ/05/2019
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ሎት-5 የትራንስፖርት አገ/ት የሚሰጥ 63 ሰው የመጫን አቅም ያለዉ 2012 ሞዴል ደረጃ-1 የሆነ አዉቶብስ መኪና፣ ለስራ ክፍል ኃላፊዎች የትራንስፖርት አገ/ት የሚሰጥ 15 ሰው የመጫን አቅም ያለዉ 2014 ሞዴል ደረጃ-1 የሆነ ሀይሩፍ መኪና እና ለካምፐሱ የጭነት አገ/ት የሚሰጥ አይሱዙ የጭነት መኪና ሞዴሉ 2012 እና ከዛ በላይ የሆነ መኪና ኪራይ ግዥ ለሁለተኛ ዙር እና ሎት-6 የቲማቲም ድልህ ለመጀመሪያ ዙር በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አሳዉጆ ህጋዊ ከሆኑ ነጋዴዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫረቾች፡-
ሎት-5 የሚወዳደሩ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
- በዘርፉ አግባብነት ያለዉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ያለው(ያላት)
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN No/ያለዉ(ያላት)
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ/ የሆነች
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/ትችል፤
- የመኪናው ባለቤትነት ሊብሬ ወይም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ የሚችል(ትችል)
- የተሽከርካሪው ወቅታዊ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጀ ያለው(ለት)
- ለተሽከርካሪው የሦስተኛ ወገንና ሙሉ ኢንሹራንስ ያለው (ለት)
- የተሽከርካሪው ወቅታዊ የቴክኒክ ምርማራ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል(ትችለ)
- መኪናው ደረጃ-1 የሆነ
ከሎት-1 እስከ 4 የሚወዳደሩ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
- በዘርፉ አግባብነት ያለዉ እና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለዉ(ያላት)
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN No/ ያለዉ(ያላት)
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/ትችል፤
- የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/ትችል፤
- ከዚህ በፊት በዘርፉ ያገለገሉበት የመልካም ስራ አፈጻጸም ምስክር ወረቀት ያለዉ/ያላት/
- ከላይ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫረቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ጨረታ በሀገር አቀፍ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ ከግዥ ቡድን መሪ ቢሮ በአካል በመቅረብ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል መግዛት ትችላላችሁ።
- ከተሰጠው መስፈርት ወይም የቴከኒክ ፍላጎት መግለጫ ዉጭ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከውድድር ዉድቅ ይደረገል።
- ተጫራቾች እኩል ዋጋ ቢያቀርቡ አሸናፊው በዕጣ የሚለይ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታዉን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሞልተዉ ማቅረብ አለባቸዉ።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር የተገለጹ ዕቃዎች አገ/ት የማቅረቢያ ጊዜ በዉል ስምምነት የሚገለጽ ሆኖ አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈዉን ዕቃ/አገ/ት በራሱ ትራንስፖርት እስከ ዋቸሞ ዩኒቨርሲት ዱራሜ ካምፓስ ግቢ ድረስ ያቀርባል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት፡-5 ለአዉቶብስ መኪና ለእያንዳንዱ ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) ብቻ በድምሩ ብር 200,000(ሁለት መቶ ሺህ ብር)ብቻ፣ ለሀይሩፍ መኪና ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ ብር)ብቻ እና ለአይሱዙ መኪና ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ እና ለሎት፡-6 ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ሲፕኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ሌተር/ደብዳቤ/ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በዱራሜ ካምፓስ ስም አዘጋጅተዉ ለብቻዉ በፓስታ በማሸግ ከኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የዕቃ/የአገልግሎት ዝርዝር ነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ ተደርጎ በተሰጠዉ ዕቃ/አገ/ት ግዥ ዝርዝር ገጽ ወይም በራሰችሁ ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ቅደም ተከተሉን ሳያዛቡ በመሙላት የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በሁሉም ገጾች ላይ በማሰረፍ 1/አንድ/ ኦርጅናል እና 2 (ሁለት) ፎቶ ኮፕ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛዉቀን ከጧቱ እስከ 4፡15 ድረስ ፖስታዉን በማሸግ በዋቸሞ/ዩ/ዱ/ካ ግዥ ቡድን መሪ ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገበት ይጠበቅባቸዋል። ጨረታዉ በ11ኛዉ ቀን ከቀኑ 4፡15 ላይ ታሽጎ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በዚያዉ ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል። ይሁን እንጂ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጨራቾቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በራሳቸዉ ፍላጎት አለመገኛት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም። ነገር ግን 11ኛዉ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል። ጨረታዉ የታወጀበት ቀን 12/01/2019 ዓ/ም ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን 22/01/2019 ዓ/ም ይሆናል።
- የጨረታው ውጤት ጨረታው ተገምግሞ እንዳለቀ በደብዳቤ /በፋክስ/ በስልክ እና በዉስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል።
- ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና (ዉል ማስከበሪያ) በቅድሚያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛዉም ተጫራች በውል ውስጥ የተካተቱትን ህጎች የማክበር ግዴታ አለበት።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ሎቶች ዋጋቸውን ሲሞሉ ከቫት ጋር ወይም ያለቫት ብለዉ መግለጽ አለባቸው። ካልሆነ ግን የተሞላው ዋጋ ቫት 15% እንዳለ ተደርጎ ይወሰደል።
- በዋጋ ማቅረቢያው ላይ የሚጻፈዉ ጽሁፍ በግልጽ የሚነበብ መሆን አለበት። ድልዝ ስርዝ ቢኖር እንኳን ማስተካከያ በተደረገዉ ቦታ ላይ የድርጅቱ ህጋዊ ፊርማ መፈረም አለበት።
- በተጨማሪ የእያንዳንዱ ዕቃ/ አገልግሎት ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ ተገልጾአል።
- ካምፓሱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ መረጃ፡- ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር፡- 09 16 72 60 33 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 10:15
- Bid opening: 2026-10-02 14:30
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Wachemo University Durame Campus
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T10:42:37.000Z
- Source: 2merkato