Machinery
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ (ዋና መስረያ ቤት) የሚገኙ የሽያጭ ማሽኖች የጥገና እና የማሻሻያ (ማዘመን) በድጋሜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ (ReBid for Vending Machine Repair and Upgrade) ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
በድጋሜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:-SSNT-T643
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ (ዋና መስረያ ቤት) የሚገኙ የሽያጭ ማሽኖች የጥገና እና የማሻሻያ (ማዘመን) በድጋሜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ (ReBid for Vending Machine Repair and Upgrade) ሥራዎችን ለማቅረብ ፈቃደኛ ለሆኑ ብቁ የአገልግሎት አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-
- በሽያጭ ማሸኖች የጥገና ፤ የማሻሻያ (ማዘመን) እና ተዛማጅ አገልግሎቶች ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፤ የግብር ከፋይ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፍቃድ ያላቸው ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T643 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ የጨረታ ቁጥሩን፣ የድርጅታቸውን ስምና ስልክ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) “በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ” ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል ሰኞ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡ዐዐ ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ:
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
አሸብር ተሾመ በስልክ ቁጥር፡ +251-15-17-49-18 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
ኢሜል: [email protected]
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
Ethiopian
የኢትዮጵያ
Tender details
- Deadline: 2026-10-26
- Bid closing time: 15:00
- Bid opening: 2026-10-26 15:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
- Buyer TIN: 0000028498
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T12:45:45.000Z
- Source: 2merkato