Installation, Maintenance and Other Engineering Services
የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ የኮንስትራክሽን መምሪያ የነቀምት ምዕራብ ግንባር የሰራዊት ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚዉሉ በየዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ የህንፃ ሥራ ተቋራጭ ድርጅቶች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በመሃንዲስ ዋና መምረያ ኮንስትራክሽን መምሪያ ነቀምት ምዕራብ ግንባር የሠራዊት ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጄክት ግዥ ክፍል
በሀገር ውስጥ ለሚፈፀሙ የህንፃ ሥራ ተቋራጭ እና ተዛማጅ አገልግሎቶች ግዢ የሚውል
መደበኛ የጨረታ ሰነድ
የህንፃ ሥራ ተቋራጭ
|
1.0 |
CONCRETE WORK |
|
2.0 |
BLOCK WORK |
|
3.0 |
ROOF WORK |
|
4.0 |
Sanitary Installation |
|
5.0 |
Electrical installation |
|
6.0 |
FINISHING WORK |
የግዢው መለያ ቁጥር መሃ/ዋ/መ/ኮንሰ/መ/ነ/ምዕ/ግ/የሠ/ሆ/ግ/ጨ/ቁ 02/2019
የግዥው ዘዴ ግልፅ ጨረታ
የጨረታ ሰነዱ የሚወጣበት ቀን በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን መስከረም 12/2019 ዓ/ም ጀምሮ ነው
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መ/ቁጥር መ/መ/ዋ/መ/ኮ/ መምሪያ⁄ ነቀምት ምዕራብ ግንባር የሠራዊት ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት ግ/ጨ/ቁ 02/2019 የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ የኮንስትራክሽን መምሪያ የነቀምት ምዕራብ ግንባር የሰራዊት ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚዉሉ በየዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ የህንፃ ሥራ ተቋራጭ ድርጅቶች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በዚሁም መሰረት በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች
የግምገማ እና የብቃት መስፈርቶች
ይህ ክፍል የተጫራቾች መመሪያ ክፍል 1 እና ክፍል 2 ያካተተ ነዉ። ተፈላጊዎቹ ብቃቶች ያሉት ስለመሆኑ ለመገምገምና ለመወሰን መጠቀም ያለበትን ሁሉንም ነጥቦች ዘዴዎችና መስፈርቶች ይይዛል። ሌሎች ማንኛቸውም ነጥቦች ዘዴዎች ወይም መስፈርቶች ጥቅም ላይ አይውሉም።
1. የብቃት መስፈርቶች
ተጫራች ድርጅቶች ማሟላት ያለባቸው ነጥቦች
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ በ2018/2019 የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
- በዘርፉ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው
- የተጫማሪ እሴት ታክስ (value added tax) ተመዝጋቢ የሆኑ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- ደረጃ ሦስት (3) እና ከዛ በላይ የሆኑ የህንፃ ስራ ተቋራጭ
- ኦንላይን ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ
- ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
- ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተረጋገጠ የ2018./2019 ዓ/ም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የዘጠኝ ወር ተመላሽ ያደረጉበትን ማስረጃ ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ (በኮፒው ጀርባ ላይ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ኦሪጅናል ማህተም የተደረገበት መሆን አለበት)
- በመንግስት መስሪያ ቤቶች ጨረታ እንዳይሳተፉ ያልታገዱ
- ተወዳዳሪዎች በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ግዢ ቡድን ከዚህ በፊት ተወዳድሮ ያሸነፋበትን ስራዎች በውሉ መሰረት ሙሉ በሙሉ ያሰረከቡ ወይም የተጠቃሚ ክፍል አቤቱታ ያልቀረበባቸው መሆን አለባቸው።
- ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በክፍል 2 በተገለጸው መሠረት በጀርባው የባንኩ ማህተም ያለው የተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችሉ
- ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶች ለብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
- ቴክኒካል ዶክመንት ተገምግሞ ያለፈ ድርጅት ብቻ ፋይናንሻል ይከፈታል
- በኮንስትራክሽን ሳይት ላይ ኮንክሪት ባቺንግ ፕላንት፣ ክሬሸር፣ ኮንክሪት ፓምፕ መግጠም አና ማስተዳደር የሚችል እና ሰርቲፊኬት ወይም ላይሰንስ ሊኖረው ይገባል።
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ቅጂ (ኮፒ) ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች እንደ አስፈላጊነቱ ከላይ የተጠቀሱት የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ኦሪጅናል ሲጠየቁ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ፣ ፍቀት ወይም ፍሉድ ካለ ጨረታዉ ውድቅ እንዲሆን ይደረጋል።
ተጫራቾች በውሉ መሰረት ስራውን አከናውነው ህጋዊ ማስረጃ ሲያቀርቡ ህጋዊ የዱቤ ሸያጭ ደረሰኝ እና በኢ/ያ ንግድ ባንክ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸዉ።
ከላይ የተጠቀሱትን እሰከ ጥቅምት 02 ዕለት ድረስ ዘወትር በሥራ ቀናት ከ2፡00 ሰዓት እሰከ 11፡00 ሰዓት ባለ ጊዜ ውሰጥ በመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ ኮንስትራክሽን መምሪያ ነቀምት ምዕራብ ግንባር የሰራዊት ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት በመቅረብ ለዚህ ጨረታ በአማርኛ የተዘጋጀውን ዝርዝር መረጃ የያዘ ጨረታ ሰነድ 500.00/አምስት መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል ገዝተው መወዳደር ይቸላሉ።
የጨረታ ሳጥን መሀንዲስ ዋና መምሪያ ኮንስትራክሽን መምሪያ ነቀምት ምዕራብ ግንባር የሰራዊት ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጄክት ሲሆን የሰነድ ማስገቢያው ግዜም የጨረታ ሰነድ ከተገዛበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 02 ዕለት ድረስ ሲሆን የመክፈቻ ቀንና ሰዓት፡ ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል።
❖ የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ ዘግይቶ የሚደርስ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
❖ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ነቀምት ምዕራብ ግንባር የሰራዊት ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት ግቢ ልዩ ቦታው (ጉቴ)
ስልክ፦ 09 13 15 85 12/ 09 11 26 67 98
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመሃንዲስ ዋና መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-10-12
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-12 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ministry of Defense
- Buyer address: መከላከያ ት/ስልጠና ዋ/መ/ግዥ ቡድን ጃል ሜዳ ታቦት ማደሪያ ፊት ለፊት
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T12:56:30.000Z
- Source: Qelal Tenders