Printed Advertising Materials
በጉለሌ ክ/ከተማ የማይጨው ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል
Printed Advertising MaterialsAdvertising and PromotionPrinting and Publishing
Addis Ababa
More tags
StationeryOffice Supplies and ServicesChemicals and ReagentsLaboratory Equipment and ChemicalsEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsHand Tools and Workshop EquipmentHealth Related Services and MaterialsHealth Care, Medical IndustryMedical Equipment and SuppliesPharmaceutical ProductsOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurnitureFreight TransportWarehousing, Transit and Transport ServiceVehicleRentVehicles PurchaseShoes and Other Leather ProductsTextile, Garment and LeatherTextile, Garments and UniformsOffice Machines and ComputersMaintenance and RepairOthersCleaning and Janitorial Equipment and ServiceComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesTransportation ServiceInstallation, Maintenance and Other Engineering ServicesAmharic2merkatoGulele Sub City Mayechew Health Offce
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ጉ/ክ/ከ/ማ/ጤ/ጣ 001/20219
በጉለሌ ክ/ከተማ የማይጨው ጤና ጣቢያ
- የህትመት ውጤቶች፣
- አላቂ የጽህፈት ዕቃዎች፣
- የጽዳት ዕቃዎች፣
- የላቦራቶሪ ዕቃዎች፣
- አላቂ የጥገና ዕቃዎች፣
- የመድሃኒት እና የህክምና ዕቃ፣
- የፈርኒቸር ዕቃዎች፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- ለጭነት አገልግሎት የሚውል
- መኪና እንዲሁም MR1 ዝርጋታ፣
- የደንብ ልብስና ኮንፒውተር ጥገና፣ የደንብ ልብስ ስፌት ለማሰፋት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ።
እያንዳንዱ የጨረታው ተሳታፊ የሚከተሉትን የጨረታ መመሪያ ነጥቦችን በመረዳት ሰነዶች ላይ እንዲያሟሉ ማድረግ ይገባቸዋል።
- በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ።
- የግብር ከፋይነት ቲን ነምበር መዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው።
- የምዝገባና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 04 የእለት ገንዘብ ተቀባዮች ጋር በመቅረብ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚሸጡበትን ነጠላ ዋጋ እና ቫትን ጨምሮ ጠቅላላ ዋጋውን በግልጽ ማስፈር አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር/10/ ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የሚያቀርቡትን የዋጋ ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ እንዲሁም (CPO) እራሱን በቻለ በተለያየ ፖስታ ለየብቻው በማሸግ በተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪ ለደንብ ልብስ ጠቅላላ ዋጋ 5,000/አምስት ሺህ ብር ደንብ ልብስ ስፌት 3,000/ ሶስት ሺህ ብር ለአላቂ የቢሮ ዕቃ 3,000/ሶስት ሺህ ብር/ ጽህፈት 3,000 ለህትመት 3,000/ ሶስት ሺህ ብር ለመድሃኒትና ላብራቶሪ ሪኤጀንት እንዲሁም ህክምና ዕቃ 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር/ ለፅዳት ዕቃ 4,500 /አራት ሺህ አምስት መቶ ብር/ ለጥገና ዕቃ 3,000 /ሶስት ሺህ ብር ፣ ለፈርኒቸር ዕቃ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ እና MR ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 30,000(ሰላሳ ሺህ ብር) ለጭነት አገልግሎት የሚውል መኪና 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) የኮንፒውተር ጥገና 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት (CPO) /ቢድ ቦንድ የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን።
- በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ 10ኛው ቀን እስከ ከሰዓት 11፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 407 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት አለባቸው። ጨረታውም በ10ኛው ቀን ከሰዓት 11፡00 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ጨረታው የሚከፈት ይሆናል። ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት 3፡00 በማይጨው ጤና ጣቢያ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል ተጨራቶች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በተቀመጠው ቀንና ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ እንዲያስገቡ ሲጠየቁ በወቅቱ በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል 3ተኛ ፎቅ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ባቀረቡት ናሙና ኮሚቴው በጥራትና በዋጋ የተሻለውን ይመርጣል ናሙና ያልቀረበበት ዕቃ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- የተጫራቾች ሙሉ ስማቸው፣ አድራሻቸው፣ ፊርማቸውን እና ማህተባቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ማስፈር ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ፖስታ ላይ ለየትኛው ሎት እንደሚወዳደሩ በግልፅ ለይተው መፃፍ አለባቸው።
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ለናሙና ያቀረቡትን ዕቃ በጊዜ ካልወሰዱ ከ6ወር በላይ ከቆየ ለመንግስት ውርስ ይደረጋል።
- ጨረታ ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ወይም። ከጨረታ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ።
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ከመ/ቤታችን ውል ተዋውሎ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% ማስያዝ ይኖርበታል። ይህ ባይሆን ግን በጨረታው የተያዘው ቼክ ወይም ሲፒኦ በቀጥታ ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛል።
- ማንኛውም ተጫራቾች በሚያቀርቡት የዋጋው ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ቫትን አካቶ መስራት ይኖርባቸዋል። ይህ ሆኖ ባይገኝ ግን ተጫራቹ እንዳካተተ የቆጠርለታል።
- ጤና ጣቢያው ከአሸናው ድርጅት ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ በተገለጠ የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ከውል በፊት እስከ 20% መጨመር ወይም 20% የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በግምገማ ወቅት እኩል ውጤት ያመጡ ተወዳዳሪዎች በእጣ የሚለዩ ይሆናል።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
- ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ለሚወዳደርበት ዕቃ ካደራጃቸው የመንግስት ተቋም ለግዥ ፈጻሚው መ/ቤት የተጻፈ ደብዳቤ በመያዝ በሚያመርቱትና እሴት ለጨመሩበት ላይ ብቻ የሚወዳደሩ መሆን አለበት።
- አድራሻ 6ኪሎ ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት አለፍ ብሎ ግብፅ ኢንባሲ ፊትለፊት ወይም
በስ.ቁ 0111-54 20-68 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
በጉለሌ ክ/ከተማ የማይጨው ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ጨረታ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከሰዓት 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-03 09:00
- Bid opening (note): ጨረታ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Gulele Sub City Mayechew Health Offce
- Buyer address: 6ኪሎ ኢንተርናሽናል ሊደር ሽፕ ኢንስቲትዩት አለፍ ብሎ ግብፅ ኤምባሲ ፊት ለፊት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር በየሎቱ
- Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T13:20:44.000Z
- Source: 2merkato