Food and Beverage

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት የፀጥታ ሃይል አገልግሎት የሚዉል ጋሌጣ ብስኩት በነጠላ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አመታዊ ዉል በመያዝ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ግጨ03/2018

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በ2019 በጀት አመት ለዋና ጠቅላይ መምሪያዉ በግዳጅ ላይ ለሚገኘው የክልሉ የፀጥታ ሃይል አገልግሎት የሚዉል ጋሌጣ ብስኩት በነጠላ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አመታዊ ዉል በመያዝ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1.  ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና የሚወዳደሩበት ሎት ጠቅላላ ዋጋ ከ500,000 (አምስት መቶ ሽህ) ብር በላይ ከሆነ የቫት የሚችል ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ከምግብና መድሃንኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የታደሰ የጥራት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የተጫራቾች መመሪያውንና ብስኩት የሚቀርብበትን ቦታዎች የሚገልጽ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀኖች ውስጥ ለእያንዳንድዱ ዝርዝር ሰነድ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል በአማራ ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 13 መግዛት ይችላሉ፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ከፈለጉ ማስረጃውን (የገቢ ደረሰኙን ) ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከፋይናንስ (ዋጋ ማቅረቢያ) ጨረታ ሰነድ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸል፡፡
  5. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በተጫራቾች መመሪያ ላይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
  6.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ላይ በእያንዳንዱ ገፅ ማህተማቸውንና ፊርማችን በማሰፈርና ፖስታውን በሚገባ በማሸግ የአማራ ፖሊስ ዋናዉ መስሪያ ቤት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 06 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከምሽቱ 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11፡00 የሚዘጋ ሲሆን በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  8.  የርክክብ ቦታው በተገለፀው የማቅረቢያ ቦታ ድረስ በግንባር የሚቀርብ ይሆናል፡፡
  9.  መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ፡-በስልክ ቁጥር 09 18 02 81 75/09 13 03 30 58 ባህር ዳር ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት
ባህር ዳር


Tender details

  • Deadline: 2026-09-30
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11፡00
  • Bid opening: 2026-10-01 10:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11፡00 የሚዘጋ ሲሆን በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ
  • Bid bond: 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን ብር)
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Be'kur (Sep 21, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T13:50:10.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders