Land Lease & Real Estate

የአዳማ ከተማ አስተዳደር በከተማ አስተዳደሩ በመኖሪያ ቤቶች ላይ የሚስተዋለውን የፍላጎትና የአቅርቦት አለመጣጣም ችግር ለመፍታት ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቶ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲችል በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በቦሌ ክፍለ ከተማ አንዶዴ ወረዳ ተገንብተው የተጠናቀቁ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በካሬ የመነሻ ዋጋ በግልፅ ጨረታ መግዛት ለሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም የግል ወይም

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዳማ ከተማ አስተዳደር በከተማ አስተዳደሩ በመኖሪያ ቤቶች ላይ የሚስተዋለውን የፍላጎትና የአቅርቦት አለመጣጣም ችግር ለመፍታት ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቶ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲችል በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በቦሌ ክፍለ ከተማ አንዶዴ ወረዳ ተገንብተው የተጠናቀቁ ባለ 5 ወለል በቂ የመኪና ማቆሚያ የ24 ሰዓት የውሃ እናመብራት አገልግሎት፡ ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ፡ በቂ የልጆች መጫወቻ ቦታ እና የጋራ መናፈሻ ቦታ ያላቸው ባለ አንድ መኝታ፣ ባለ ሁለት መኝታ እና እስቱዲዮ 539 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባሉበት ሁኔታ በካሬ የመነሻ ዋጋ በግልፅ ጨረታ መግዛት ለሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም የግል ወይም የመንግስት ድርጅት ወይም አክሲዮን ማህበር አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል።

ስለሆነምማንኛውምለጨረታየቀረቡየመኖሪያቤቶችንለመግዛትየሚፈልግ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ፣ የግል ድርጅት ወይም ለሰራተኞቻቸው መግዛት የሚፈልጉ የመንግስት ወይም የግል ወይም አክሲዮን ማህበራት ወይም ድርጅቶች ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በስንቄ ባንክ የአካውንት ቁጥር 1054551161211 በመክፈል ፖስታ  ቤት አከባቢ በሚገኘው ትልቁ ህንፃ በአዳማ ከተማ ገንዘብ/ፅ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ግዢ ክፍል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።

ጨረታው የሚከፈተው በ22 ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡00 ጀምሮ በተጫራቾች መመሪያ ላይ በተገለፀው ፕሮግራም መሰረት ይሆናል፣ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በተከታዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በ 0938-70-91-02 ይደውሉ

የአዳማ ከተማ አስተዳደር


Tender details

  • Deadline: 2026-10-16
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-17 09:00
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22 ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Adama City Administration
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 23, 2026)
  • Posted at: 2026-09-23T08:29:54.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders