Food and Beverage
ፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ ሕብረት ሥራ ማህበር በ2019 ዓ.ም. በዓመት ውስጥ ሊገዛቸው ያሰባቸውን የተለያዩ ግብዓቶች በትስስር እና በጥቅል ግዥ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ ሕብረት ሥራ ማህበር በ2019 ዓ.ም በዓመት ውስጥ ሊገዛቸው ያሰባቸውን የተለያዩ ግብዓቶች በትስስር እና በጥቅል ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የሎት ቁጥር |
የዕቃው ዝርዝር |
|
1 |
ሎት 1 |
የስቴሽነሪ እቃዎች |
|
2 |
ሎት 2 |
የበግ ስጋ አቅራቢዎች |
|
3 |
ሎት 3 |
እንስሳትና የእንስሳት ተዋፅኦ አምራቾችና አከፋፋዮች (ወተት፣ ቅቤ፣ አይብ፣ እንቁላል እና አሳ) |
|
4 |
ሎት 4 |
ሚጥሚጣ እና የበርበሬ ቅመም ግዥ |
|
5 |
ሎት 5 |
የፅዳት እቃዎች |
|
6 |
ሎት 6 |
ከሰል አቅራቢ |
|
7 |
ሎት 7 |
የኳስ ሜዳ ሳር እድሳት ከነ ባለሙያው |
ተጫራቾች
1. በዘርፉ የታደሠ ህጋዊ የንግድ የሥራ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ወቅታዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ፣ የቫት የተጨማሪ እሴት /ታክስ ምዝገባ እንዲሁም ሎት 2 ፣ ሎት 3 ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች ሠነድ ሊወስዱ ሲመጡ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሠነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፤
4. ከላይ የተዘረዘሩ መረጃዎችና ሰነዶች አሟልተው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በስምንተኛው ቀን 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ሻላ 17/17 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ይከፈታል፡፡ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሣጥን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓትን አያስተጓጉልም።
6. አሻሚ፣ የተሰረዘ፣ የተደለዘ እና ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ የጨረታ ዋጋ በመሙላት መወዳደር ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፤
7. የሚወዳደሩባቸውን እቃዎችና ናሙና ጨረታው በሚከፈት ቀን በዝርዝር ማቅረብ አለባቸው።
8. በጨረታው አሸናፊ ለሆኑባቸው ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 2% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከድርጅቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
9. በዓመት ውስጥ ሊገዙ የታሰቡትን ግብዓቶች ዓመታዊ ትስስር ይፈፅማል።
10. የጨረታውን መመሪያ አለማክበር ከጨረታው ያሰርዛል፤
11. ፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላ/የተ/የህ/ሥ/ማህበር ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ሥራ ማህበር 17/17 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ሻላ መናፈሻ ቅጥር ግቢ ውስጥ የማዕከሉ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቀርበው ሠነዱን መግዛት ይቻላል።
ለበለጠ 0116 184 076 / 0116 187 529 / 0116 631 244
ፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላ/የተ/የህ/ሥ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-09-30
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡00
- Bid opening: 2026-10-01 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስምንተኛው ቀን 4፡00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Fana Bole Consumer Cooperative Association
- Buyer address: ሻላ መናፈሻ ከአትላስ ከፍ ብሎ ቦሌ ወረዳ 03 አስተዳደር ቢሮ
- Bid bond: 5,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 23, 2026)
- Posted at: 2026-09-23T10:00:14.000Z
- Source: 2merkato