Vehicles Purchase
የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ /መኢኢግ/ ሃይብሪድ ተሽከርካሪ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Description
በድጋሜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ መኢኢግ/ግጨተሽ/05/2019
1. የግዥ ፈፃሚው ስም: መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ/መኢኢግ /
2. የግዥው ዓይነት: ሎት አንድ ሃይብሪድ ተሽከርካሪ ግዥ
3. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡- በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN Number) እና አቅራቢነት ኦን-ላይን የተመዘገበና የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
4. የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ፡- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ ግሩፕ በአቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 102 እና 105 ሀይሌ ጋርመንት የቀድሞ ሪቬራ ሆቴል ማግኘት ይችላሉ፡፡
5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በእያንዳንዱ በሚወዳደሩበት ሎት ላይ ለተጠቀሰው ጠቅላላ ዕቃ የጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተወሰነ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Performance bond) ተጫራቹ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% (10 ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ሲያቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወዲያው ይለቀቅለታል፡፡
7. የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ የሚከፈል የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በገንዘብ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይቻላል፡፡
8. የመወዳደሪያው ሰነድ የሚቀርበው ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል፣ ፋይናንሻል ሰነድ ኮፒ እና ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ የቅጂ ብዛት ለእያንዳንዱ ሰነድ አንዳንድ ኮፒ ሆኖ ሰነዶቹ ሥልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸውና የድርጅቱ ማህተም ያለባቸው መሆን አለባቸው፤ እንዲሁም ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዕቃዎች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል መግለጫ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በግልፅ ከላይ በሚታይ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ብለው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች በቀረቡት መወዳደሪያ ሀሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
10. ጨረታው ለተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ጊዜ፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ከጠዋት 2፡30 እስከ 10፡30 የስራ መውጫ ባሉት ሰዓቶች ሲሆን ጨረታው የሚዘጋው በቀን 29 መስከረም 2019 ከጠዋት 4:30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያኑ ቀን 29 መሰከረም 2019 ከጠዋት 4:40 ይከፈታል፡፡
11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠውን ስፔስፊኬሽንም ሆነ የዕቃ ዓይነት ከሌለው የለንም ወይም ሰረዝ(--)ማድረግ እንጂ በአማራጭ መሙላት አይችልም፡፡
12. ግሩፑ በጨረታ ሰነዱ በሎት አንድ ላይ የተቀመጠውን የተሽከርካሪ ዝርዝር ፍላጎት በተጨማሪ በምስል ማቅረብ ይችላል፡፡
13. ግሩፑ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃ ሲፈልጉ ፡
ስልክ ቁጥር፡- 0967 261 636 / 0996 117 472
ሀይሌ ጋርመንት የቀድም ሪቬራ ሆቴል አዲስ አባባ ፣ኢትዮጵያ
የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ /መኢኢግ/
Tender details
- Deadline: 2026-10-09
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-10-09 10:40
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defense Engineering Industry Corporation
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 24, 2026)
- Posted at: 2026-09-24T08:13:09.000Z
- Source: 2merkato