Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር)፣ የፅሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና ቋሚ አላቂ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ አቅራቢ ድርጅት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር)፣ የፅሕፈት መሣሪያዎች የፅዳትና ቋሚ አላቂ ዕቃዎች፣ የደምብ ልብስ አቅራቢ ድርጅት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በየንግድ መስኩ ሕጋዊ የሆነ የንግድ ፍቃዳቸውን፣ ዓመታዊ የሥራ ግብር የከፈሉበትን፣ በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበት የሚገልፅ መረጃ ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒውን ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ከወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ክፍል በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ ጨረታ ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 10,000 (አስር ሺ) ብር በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ በማድረግ በግልጽ በመጻፍ ኮፒና ኦሪጅናሉን በመለየት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
5. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደረጁ ማኅበራት ከሆኑ በመንግሥት የግዥ መመሪያ መሠረት ይበረታታሉ።
6. ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ05፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል።
7. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ በጽሑፍ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ የጨረታ ውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ (CPO) በማስያዝ ከመሥሪያ ቤቱ ጋር መፈራራም አለበት።
8. አሸናፊው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል።
9. ያሸነፉትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ መ/ቤቱ ግምጃ ቤት ማምጣትና ፈርኒቸሮች በራሱ ወጭ መገጣጠም ይኖርባችኋል።
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፦ ስልከ ቁጥር፦ 046 443 0204፤ 09 16 37 69 061 ፣ 09 12 44 35 64
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-12
- Bid closing time: 10:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-12 11:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Bule Hora Woreda F/E/D/Bureau
- Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር) ለእያንዳንዱ ጨረታ
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 24, 2026)
- Posted at: 2026-09-24T08:31:53.000Z
- Source: 2merkato