Spare Parts and Car Decoration Materials

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የተሽከርካሪ ጎማዎች (ሎት 1)፣ የፕሪንተር እና ፎቶኮፒ ማሽን ዕቃዎች (ሎት 2)፣ የስቴሽነሪ እና ፅዳት ዕቃዎች (ሎት 3) ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ፕሪንተር፣ ፎቶኮፒማሽን ፣ የፅዳት ዕቃዎች እና ስቴሽነሪ ዕቃዎች ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

ለአገልግሎት መ/ቤታችን ስራ አገልግሎት የሚውል የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ፕሪንተር፣ ፎቶኮፒ ማሽን ፣ የፅዳት ዕቃዎች እና ስቴሽነሪ ዕቃዎች ከዚህ በታች በተጠቀሱት ሎቶች መሰረት ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የሎት (Lot) ቁጥር

የዕቀዎቹ ዓይነት

1

ሎት አንድ

የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች

2

ሎት ሁለት

የፕሪንተር እና ፎቶኮፒ ማሽን ዕቃዎች

3

ሎት ሶስት

የስቴሽነሪ እና ፅዳት ዕቃዎች

በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የሚፈለግባቸውን ማንኛውንም የመንግሥት ግብር አጠናቅቀው ለመክፈላቸው ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ፣ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ በጨረታ ለመሳተፍ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን በአቅራቢነት የተመዘገቡ እንዲሁም የተ.እ.ታ.ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን፣ በብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ውል በመግባት የሚፈፀም ይሆናል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

1) የጨረታ ሰነዱን ጉለሌ እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ ፖሊስ መኮንኖች ክበብ ፊትለፊት ከሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና መ/ቤት የፋይናንስ ቡድን ቢሮ በመምጣትና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ለ10 ተከታታይ ስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ፣ ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 ባለው ጊዜ ውስጥ መግዛት ይቻላሉ። ቅዳሜና እሁድ የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ስራ ቀናት አይደሉም።

2) ማንኛውም ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጥቅል ዋጋ 2 /ሁለት/ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በEDRE Refugees and Returnees Service ስም በተዘጋጀ የባንከ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በቅድመ-ሁኔታ ያልተገደበ የባንክ ዋስትና ደብዳቤ፣ የአገልግሎቱን ዋጋ፣ በቀረበው ዝርዝር የፍላጎት መግለጫ መሰረት የቴክኒክ ሰነድ እና እንዲሁም በጨረታ ሠነዱ የተዘረዘሩትን የብቃትና የልምድ ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚያያዙ ማስረጃዎች በሙሉ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያላበቃላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

3)የመጫረቻ ሠነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 10ኛው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ከታች በተመለከተው አድራሻ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአገልግሎት መስሪያ ቤቱ የሰራተኞች ክበብ ምድር ቤት ይከፈታል። ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ፣ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይሆናል።

4)ለፅዳት እና ስቴሽነሪ ዕቃዎች የጨረታው መዝጊያ ግዜ ከመጠናቀቁ በፊት ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

5)መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ ከፌዴራል

ፖሊስ ክበብ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር /0943-01-29-44/09-97-23-66-31

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-20
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 10ኛው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-20 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 10ኛው የስራ ቀን 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Refugee and Returnee Service
  • Buyer's registered address: ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ላይ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
  • Posted at: 2026-11-10T08:25:42.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders