Machinery and Equipment
ላየንስ አግሪ-ሜክና ኢንጅነሪንግ አገልግሎት ያገለገሉ መኪናዎች፣ የእርሻ ማሽነሪዎች እና ልዩ ልዩ ዕቃዎችና መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ቁጥር ፡- LAMES/B/011/2019
ላየንስ አግሪ-ሜክና ኢንጅነሪንግ አገልግሎት ያገለገሉ መኪናዎች የእርሻ ማሽነሪዎች እና ልዩ ልዩ ዕቃዎችና መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
- በመሆኑም የዘመኑን ግብር የገበሩና ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ግለሠቦችና ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ
- ጨረታው እስከ ህዳር 17 ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ድረስ አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው የሚዘጋው በዛው ቀን 4፡00 ሰአት ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል እቃዎችን የድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ማየት የሚቻል ሲሆን ጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ቢሾፍቱ ድረስ መምጣት ለማይችል ተጫራች የጨረታ ሰነድ መግዣውን ከስር በተጠቀሰው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የባንክ አድቫይሱን በሞባይል ቁጥር፦ 0910-611842/0912047510 ቴሌግራም ላይ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ሶፍት ኮፒ በቴሌግራም ማስላክ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ተሸከርካሪዎች እና መለዋወጫዎች ጨረታ ሰነዱ ከገዙበት ቀን ጀምሮ ቢሾፍቱ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ ላየንስ አግሪ-ሜክና ኢንጅነሪንግ አገልግሎት ቢሾፍቱ/ባቦጋያ ከጤና ጣቢያ ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ግቢ በአካል ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ሊገዙ የሚችሉበትን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ለእያንዳንዱ እቃ የሚሰጡትን ዋጋ በተናጠል በመሙላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚሳተፉበት እቃዎች እና መለዋወጫዎች ጠቅላላ የሰጡት ዋጋ 10% የጨረታ እና የውል ማስከበሪያ በሲፒኦ አሰርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃዎች ዋጋ በዝርዝር በመግለፅ በመሙላትና በታሸገ ፖስታ በማድረግ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ላየንስ አግሪ-ሜክና ኢንጅነሪንግ አገልግሎት ባቦጋያ ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት ባለው በቴክኒክና ጥገና ክፍል ዘወትር በሥራ ሠዓት ከ2፡30 – 6፡30 እና ከ7፡30 –11፡00 ማስገባት ይችላሉ
- ከሎት አንድ እስከ ሎት ሃያ ሰባት ድረስ ለተጠቀሱት ያገለገሉ መኪናዎች እና የተለያዩ እቃዎች ተጫራቾች አንድ ሎት እና ከዛ በላይ ለመግዛት መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- የጨረታ ሰነዱን ክፍያ ዋጋ በአካውንት ማስገባት ለምትፈልጉ በንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000202429819 እና በቴሌ ብር 0920164748
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0912047510/0910946540/0913651125/0924612455 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
- ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0912047510/0913651125/ 0910946540 ወይም 0924612455 መደወልና መረዳት ይችላሉ። የባንክ አካውንት ቁጥር 1000202429819
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
ላየንስ አግሪሜክና ኢንጂነሪንግ አገልግሎት ሰርቪስ
Tender details
- Deadline: 2026-11-26
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-26 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ላየንስ አግሪ-ሜክና ኢንጅነሪንግ አገልግሎት ሰርቪስ
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
- Posted at: 2026-11-10T08:42:24.000Z
- Source: Qelal Tenders