Vehicle

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የፒክ አፕ መኪና፣ የሚዲባስ መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2019

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የግዥና ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በ2019 በጀት ዓመት የመኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1. ሎት 1 የፒክ አፕ መኪና፣ የሚዲባስ መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-

  1. በህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ
  2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ከገቢዎች የተወዳዳሪነት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፣
  5. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /Tin No/ ያላቸው፤
  6. በመንግስት ግዥና የንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ (www.PPA.gov.et)
  7. ተጫራቾች የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ/CPO/
    • ሀ. የፒክ አፕ መኪና በኤሌክትሪክ-20,000 ብር (ሃያ ሺ ብር ብቻ) CPO
    • ለ. የሚዲባስ መኪና -20,000 ብር (ሃያ ሺህ ብር ብር) CPO
    • ሐ.  የፒክ አፕ መኪና በነዳጅ –20,000 ብር (ሃያ ሺህ ብር ብቻ CPO
  8. ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በመ/ቤታችን ስም CPO ማስያዝ አለባችሁ ነገር ግን CPO ያላስያዝ ቢኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል፣
  9. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመወዳደር ጨረታው ከተዘጋጀ በኋላ የሚወዳደሩበት በተሰጠው በእስፔስፍኬሽን መሰረት መቅረብ አለበት፤
  10. ማንኛውም ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ 15ኛ ፎቅ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብና የማይመለስ 300 ብር ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣
  11. አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ወይም አገልግሎት ካቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፡፡
  12. መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፤
  13. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ኦርጅናልና እና ኮፒ ከዛ ደግሞ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ዋጋ ሞልታችሁ በተናጠል ለየብቻ በፖስታ አድርጋችሁ የድርጅታችሁን ማህተምና ፊርማ የተወዳደራችሁበትን የሎት አይነት በፖስታው ላይ እየነፋችሁ አስገቡ ካልጻፋችሁበት ደግሞ ፖስታችሁ አንደማይከፈት እያወቃችሁ የተባሉትን በሙሉ በማድረግ በግዥና  ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወደ ህንጻው ስትገቡ በቀኝ በኩል ባለው ሊፍት 15ኛ ፎቅ ፊት ለፊት ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡
  14. ጥቃቅንና አንስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸው ዕቃዎች (አገልግሎቶች) የጨረታ ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ
    • ሀ. ካደራጃችሁ መ/ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለባችሁ፣
    • ለ. ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ በመመሪያ መሰረት ለምታቀርቡት ዕቃ (አገልግሎቶች አምራች መሆን አለባችሁ፤
  15. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክክል መሙላት አለባቸው::
  16. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ዕቃ ወይም አገልግሎት ላይ ውል ሲገባ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፣እንዲሁም አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ጨረታ ተከፍቶ ውጤት ከተለጠፈ ከ8 የሥራ ቀናት በኋላ በመ ቤታችን ቀርቦ ውል መግባት አለበት፡፡
  17. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ከኛ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1.  ተጫራቾች የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑንና ያላካተተ መሆኑን መግለጽ አለባችሁ ይህ ካለሆነ ግን መ/ቤቱ ያቀረበውን ዋጋ ቫትን እንዳካተተ አድርጎ ይወስደዋል፡፡
  2. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡-አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልገሎት አስተዳደር ባስስስጣን ክፍለ ከተማ አራዳ ወረዳ፣ 1 ፒያሳ እስታቲክስ ጎን እናት ህንጻ ፊት ለፊ ዋስትና ንግድ ማእከል 15ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-011-12768-25 ይደውሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-10-06
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-06 09:30
  • Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን
  • Bid bond: 20,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 24, 2026)
  • Posted at: 2026-09-24T08:39:11.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders