Cleaning and Janitorial Equipment and Service
ሲዳማ ክልል ምክር ቤት በ2019 በጀት ዓመት የፅህፈት መሣሪያ (stationary)፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽዳት ዕቃ፣ የሲዳማ ባህል ልብስ፣ የመኪና ኮንፈርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ሲዳማ ክልል ምክር ቤት በ2019 በጀት ዓመት
- ሎት 1. የፅህፈት መሣሪያ (stationary)
- ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት 3. የጽዳት ዕቃ
- ሎት 4. የሲዳማ ባህል ልብስ
- ሎት 5. የመኪና ኮንፈርት በተገለጸው መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች ለተሰማሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ከሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በሲዳማ ክልል ምክር ቤት በግዥ ክፈ/ንብ/ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት Ground ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ ከፍለው ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
3. የጨረታ ማስከበርያ በባንክ የተረጋገጠ የተመሰከረ ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በመመሪያ መሰረት አስፈላጊውን መረጃ በማያያዝ ኦሪጅናልና ኮፒ እና የድርጅቱ ማህተም በማሳረፍ በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን ከጠዋት 4፡00-6፡00 ባለው ሰዓት ውስጥ ቢሮአችን ለዚሁ ተግባር ባዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ማስገቢያ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
5. ጨረታው በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰዓት በተገኙበት በግዥ /ከፊ/ንብ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት Ground ቢሮ ቁጥር 9 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል።
6. ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ ለቀጣይ የስራ ቀን ይተላለፋል።
7. የጨረታው አሸናፍዎች ያሸነፉበትን ዕቃ እስከ ቢሮ ድረስ ያቀርባሉ።
8. ቢሮአችን ጨረታውን አስመልክቶ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-09
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-09 14:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Sidama Region Council
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 24, 2026)
- Posted at: 2026-09-24T08:43:17.000Z
- Source: 2merkato