Others
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለመንገድ ከፈታ እና መንገድ ጥገና ሥራ ላይ የሚሠማሩ ማሽኖችን ለመከራየት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ሦስት ዞኖች ለመተከል ዞን ፤አሶሳ ዞን እና ካማሽ ዞን ውስጥ ለመንገድ ከፈታ እና መንገድ ጥገና ሥራ ላይ የሚሠማሩ ማሽኖችን ማለትም ዶዘር ብዛት 03, ግሬደር ብዛት = 04, ሩሎ ብዛት = 04 ሎደር ብዛት = 04 ገልባጭ መኪና ብዛት 12, ትንሽ መኪና ዳብል ጋቤና ብዛት= 05, ውሃ ቦቴ ብዛት= 04. ኤክስካቫተር ብዛት 04, ሎቤድ ብዛት= 01, በግልጽ ጨረታ ለመከራየት ይፈልጋል፤ አንዱን ዶዘር በሰዓት ሂሳብ ለ1500፡00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰዓት) ፤አንዱን ግሬደር በሰዓት ለ1500፡00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰዓት) አንዱን ሎደር በሰዓት ሂሳብ ለ1500፡00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰዓት) አንዱን ሩሎ በሰዓት ሂሳብ ለ1500፡00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰዓት) አንዱን ገልባጭ መኪና በቀን ሂሳብ ለ160 ቀናት ፤ አንዱን የትንሽ መኪና ዳብል ጋቤና በቀን ሂሳብ ለ160 ቀናት ፤ አንዱን የውሃ ቦቴ በቀን ሂሳብ ለ160 ቀናት አንዱን ኤክስካቫትር በሰዓት ሂሳብ ለ1500:00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰዓት)፤አንዱን ሎቤድ በአንድ ኪ.ሜትር ሂሳብ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፣
በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው በ2019 በጀት ዓመት ያሳደሱ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላችሁ እንዲሁም በአቅራቢነት የተመዘገባችሁ መሆናችሁን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
1. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ድህረ ገጽ መግለጽ የሚችሉ ፤
2. የሚያከራዩትን መሳሪያዎች የራሳቸው ለመሆኑ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ ወይም አግባብ ባለው ሙሉ የህግ ውክልና ማቅረብ የሚችሉ
3. የድርጅታቸውን (የቢሮዋቸውን) አድራሻ ማሳየት የሚችሉ የሆነ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል አስፈላጊውን ማስረጃ ከታደሰ ንግድ ፈቃድ ጋር በማድረግ አሶሳ በሚገኘው መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የግዥና ንብ/አስ/ዳ/ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ መውስድ ይችላሉ።
4. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ10 ቀናት (አስር) ቀን በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ11ኛው (አስራ አንደኛው ቀን) ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ህዝባዊ በዓላቶች እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን እንዲከፈት ይደረጋል።
5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ የፋይናንስና የቴክኒክ ዶክመንት ለየብቻዉ በማድረግ አሶሳ በሚገኘው መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የግዥና ንብ/አስ/ዳ/ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 10 ውስጥ ተዘጋጅቶ በተቀመጠው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ሲመጡ የሚያከራዩትን ማሽኖች የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር (ሊብሬ) ኮፒውን እና የውክልና ደብዳቤ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
7. የጨረታ ሰነድ በሚገዙበት ወቅት የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር (ሊብሬ) አሳይተው ካስመዘገቡት ማሽን ውጭ ጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው ቢያቀርቡ ተቀባይነት የለውም።
8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በተመለከተ፤ ለአንዱ ዶዘር ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/፤ ለአንዱ ግሬደር ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር፤ ለአንዱ ሎደር ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/፤ ለአንዱ ሩሎ ብር 80,000.00 /ሰማኒያ ሺህ ብር ፤ለአንዱ ገልባጭ መኪና ብር 70,000.00 /ሰባ ሺህ ብር/፤ለአንዱ ትንሽ መኪና ብር 30,000.00 / ሰላሳ ሺህ ብር/፤ ለአንዱ ውሃ ቦቴ ብር 70,000.00 /ሰባ ሺህ ብር፤ ለአንዱ ኤክስካቫትር ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/፤ ለአንዱ ሎቤድ ብር 80,000.00 /ሰማኒያ ሺህ ብር/፤ በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ በፖስታ ለብቻዉ በማሸግ (ከፋይናንሻል ዶክሜንት ወይም ከቴክኒካል ዶክሜንት ጋር መታሸግ የለበትም) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው። በመሆኑም ከባንክ ከተረጋገጠ CPO ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም በተጨማሪም ለእያንዳንዱ ማሽነሪ እና ተሽክርካሪ አይነት ከተጠየቀዉ ብዛት ውጭ መወዳደር አይቻልም።
9. መ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የስልክ ቁጥር፡-057 775 2622/ 09 11 13 07 61/ 09 13 25 97 92
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-10-05
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው (አስራ አንደኛው ቀን) ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-05 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው (አስራ አንደኛው ቀን) ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Beneshangul Gumuz
- Publishing entity: Benishangul Gumuz Regional State Road and Transport Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 25, 2026)
- Posted at: 2026-09-25T08:04:36.000Z
- Source: 2merkato