Accounting and Auditing, Accounting System Design

ዘ ዩዝ ፕሪንት (The Youth Print) የ2018 ዓ.ም. እ.አ.አ የአንድ ዓመት ሂሳብ በታወቀ B እና ከዚያ በላይ ደረጃ ባለው ፐብሊክ ኦዲት ድርጅት ለማስመርመር ይፈልጋል

Description

 በድጋሚ የወጣ የኦዲት አገልግሎት

ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር፡ TYP/002257/19/26

ዘ ዩዝ ፕሪንት (The Youth Print) በኢትዮጵያ ውስጥ የተመዘገበ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን አገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ግቦች ላይ እየሰራ ይገኛል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 2030 ዘላቂ የልማት ግቦች (SDGs) እና በአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ለማሳካት አዳዲስ የወጣቶች ሃሳቦችን እና ፕሮጀከቶችን በትምህርት፣ በምርምር፣ በፖሊሲ ትንተና፣ ትርጉም ያለው ውይይት እና ዓለም አቀፍ ትብብርን በመፍጠር ላይ እንዲሁም በመደገፍ ላይ ይገኛል።

ድርጅቱ የ2018 ዓ.ም እ.አ.አ የአንድ ዓመት ሂሳብ በታወቀ B እና ከዚያ በላይ ደረጃ ባለው ፐብሊክ ኦዲት ድርጅት ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ሥራውን ለማከናወን የሚጠይቁትን የገንዘብ መጠንና ሥራውን ለማጠናቀቅ የሚፈጅባቸውን ጊዜ በመጥቀስ፣ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት ከታች በተገለጸው አድራሻ መሠረት በፖስታ አሽገው በማስገባት መወዳደር ይችላሉ።

የኦዲት ድርጅቶቹ የሚከተሉትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው።

ሀ. አዲተሩ የሙያ ማረጋገጫ ያለው መሆኑ፣

ለ. የንግድ ፈቃድ ያለው መሆኑ፣

ሐ. የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆኑ፣

መ.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው መሆኑ፣

ሠ. ከፌዴራል ወይም ከክልል ኦዲተር መሥሪያ ቤት ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ ያለው መሆኑ።

አድራሻ ፡- አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ ቦሌ ክ/ከተማ ወርዳ 03 H.NO (ሃያት ሆስፒታል ጀርባ)

ለበለጠ መረጃ ፦ በስልክ ቁጥር 0947396499/0936114195 መደወል ይቻላል።

Email : [email protected] | [email protected] 

ዘ ዩዝ ፕሪንት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-02
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-10-02 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: The Youth Print
  • Published on: Addis Zemen (Sep 25, 2026)
  • Posted at: 2026-09-25T08:07:40.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders