Shoes and Other Leather Products

የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የስልጠና ግብቶች፣ የተለያዩ የቢሮ እቃዎች እና አገልግሎት ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የመለያ ቁጥር 01/2019

የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ለ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈጸሚ የሚሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የስልጠና ግብቶች፣ የተለያዩ የቢሮ እቃዎች እና አገልግሎት ስራ ከህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ በተጫረቱበት ዘርፍ የሞሉትን በባንከ በተረጋገጠ c.p.o. ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡

ሎት

የዕቃው/ የአገልግሎት ዓይነት

ጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1.

የደንብ ልብስ

10,000 (አስር ሺህ)

ሎት 2.

የፅዳት ዕቃዎች

10,000 (አስር ሺህ)

ሎት 3

የፅህፈት ዕቃዎች

10,000 (አስር ሺህ)

ሎት 4 .

የኤሌትሪክ ዕቃዎች

25,000 (ሃያ አምስት ሺህ)

ሎት 5.

የኮንስትራክሽን ዕቃዎች

25,000 (ሃያ አምስት ሺህ)

ሎት 6

የጂ.ኤም.ኤፍ ዕቃዎች

25,000 (ሃያ አምስት ሺህ)

ሎት 7

ፈርኒቸር ዕቃዎች

50,ዐዐዐ (አምሳ ሺህ)

ሎት 8

አውቶ ዕቃዎች

25,ዐዐዐ (ሃያ አምስት ሺህ)

ሎት 9

ጋርመንት እና ሌዘር ዕቃዎች

25,000 (ሃያ አምስት ሺህ)

ሎት 10

አይሲቲ ዕቃዎች

50,ዐዐዐ (አምሳ ሺህ)

ሎት 11

ቴክኖሎጂ ዕቃዎች

25,000 (ሃያ አምስት ሺህ)

ሎት 12

ሆቴል ዕቃዎች

25,000 (ሃያ አምስት ሺህ)

ሎት 13.

ህንፃ አስተዳደር ዕቃዎች

25,000 (ሃያ አምስት ሺህ)

ሎት 14.

ከተማ ግብርና ዕቃዎች

25,000 (ሃያ አምስት ሺህ)

ማሳሰቢያ፡-

ከሎት 1፣2፣3 ተራ ቁጥር ላሉት ሎቶች ሳምፕል መቅረብ አለበት በተመሳሳይ ሎት 7፣10 እና 12 ላይ ሳምፕል እና ቴክኒካል ዶክመንት መቅረብ አለበት፡፡

ከተለያዩ ህጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት መሠዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች

  1.  የታደሰ ንግድ ፈቃድ
  2.  የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆንዎ የሚያረጋግጥ ማስረጃ
  3. የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ
  4.  በዘርፉ የአቅራቢነት የምስከር ወረቀት
  5.  ቲን TiN No (ቁጥር ያላቸው::

 

  1. የጨረታ ዋጋ የሚሞላው ከልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በዝዙት ሰነድ ላይ ሲሆን የሚወዳደሩበትን ዘርፍ ሁሉንም መረጃዎች በሚገባ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም አስቸጋሪ ሁኔታ ካገጠመ የቀድሞው ቁጥር ሊነበብ በሚችልበት ሁኔታ በአንድ መስመር ብቻ ይሰርዙ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የአቅርቦት ዘርፍ ነጠላ ዋጋ እንዲሁም የግርጌ ድምር በመደመር የጠቅላላውን ዋጋ ማሳየት አለባቸው:: የሚሞሉት የነጠላና ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን /vat/ ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  3. ተጫራቾች ያቀረቡት ለቋሚ እቃ ለሚሰጠው አገልግሎት ቢያንስ የአንድ አመት ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ ኦርጂናሉንና ሌሎች ማስረጃዎችን ለብቻው በአንድ ፖስታ ሲፒኦ ደረሰኝ በአንድ ፖስታ እንዲሁም የጨረታ ሰነዱን ኮፒ ከነማስረጃ በአንድ ፖስታ በማድረግ በሚገባ በማሸግ በጀርባቸው ላይ ኦርጂናል ኮፒ እንዲሁም ሲፒኦ በሚል መግለጽ አለባቸው፡፡
  5.  ተጫራቾች የመጨረቻ ዋጋ በሞሉበት የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ እና በየደረጀው በታሸጉት ፖስታዎች ላይ የድርጅቱን የበላይ ሀላፊ ፈርማ ሥም እንዲሁም ህጋዊ ከብ ማህተም ማሳረፍ አለባቸው::
  6. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 በተዘረዘሩው መሰረት የሞሉትንና ያዘጋጁትን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አሰር የስራ ቀናት) በመንግስት የሥራ ሰዓት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀውና በኮሌጁ በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 በተቀመጠው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስጋባት አለባቸው፡፡,
  7. በተጫራቾች የተሞላው የጨረታ ዋጋ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ6o የስራ ቀናት ስልሳ/ ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታ ሂደት የማጭበርበር (የሙስና) ተግባር ሲፈጽሙ ቢገኙ ወይም ለመፈጸም ቢሞክሩ በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገው ተፈጸሚ ይሆናል።
  9. ተጫራቾች የጨረታውን ሂደት ለማዛባት ቢሞክሩ ያሲያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡ በቀጣይም በመንግስት ግዢ እንዳይሳተፉ ይደረጋል።
  10. ተጫራቾች የእያንዳንዱ እቃ የሚመለስ ናሙና ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት ለኮሌጁ ግዢ ባዘጋጀው ክፍል በአደራ ማስረከብ አለባቸው።
    • ማሳሰቢያ፡-
    • * ናሙና ሲያመጡ (ሲያቀርቡ) የድርጅቱ ማህተም መደረግ የለበትም ነገር ግን ምልክት ያቀረበ አቅራቢ የመጠው ናሙና ተቀባይነት የለውም ።
  11. ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው ተጫራች ውል እስኪገባ ድረስ ተመላሽ አይሆንም።
  12.  የጨረታ ሳጥኑን በ11ኛው (አስራ አንደኛው) የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የሚዘጋ ሲሆን የተጠቀሰው ጊዜ ካለፈ በኃላ የሚቀርቡ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም ፡፡
  13.  ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በግዢ ክፍሉ ውስጥ ይከፈታል።
  14. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት በመጀመሪያ በእቃ ጥራት ሲሆን በሁለተኛው ደረጃ የሚያቅርቡት ዝቅተኛ የዋጋ መጠን ሆኖ ሁለት ተጫራቾች እኩል ነጥብ ቢያመጡ የግዥ መመሪያና ደንብ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
  15. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10/00 (አሰር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማስዢያ C.PO/ ሲፒኦ/ የጨረታ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  16. ውል ሲፈጸምም ሆነ ከተፈጸመ በኋላ በጨረታው ሰነዱ ላይ ከሞሉት ዋጋ ውጪ ምንም አይነት ማስተካከያ ማድረግ አይቻልም፡፡
  17. አሸናፊ ተጫራቾች ክፍያ የሚፈጸምላቸው እንዲያቀርቡ የታዘዙትን እቃ በታዘዙበት ጊዜ በራሳቸው ወጪ ኮሌጁ ግቢ ውስጥ ንብረት ክፍል በማቅረብ ሙሉ በሙሉ ሲያስረክቡና የንብረት ገቢ ደረሰኝ ሲያቀርቡ ነው።በግዢ አፈጻጸሙ ላይ በደል ደርሶብኛል የሚል ተጫራች ለአቤቱታው መሰረት የሆነውን የመጨረሻ ውሳኔ ካሰወቀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 5/አምስት የስራ ቀናት ውስጥ አቤቱታውን ጨረታ ላወጣው የመንግስት መ/ቤት የበላይ ኃላፊ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የበላይ ኃላፊ መልስ ካልሰጠ ወይም በሚሰጠው መልስ ያልረካ ቅሬታ አቅራቢ ውሳኔው መሰጠት ከነበረበት ጊዜ ገደብ ማብቂያ ጅምሮ በሚቆጠር 5/ አምስት / የስራ ቀን ጊዜ ውስጥ አቤቱታውን ለአጣሪ ኮሚቴ ማቅረብ ይችላል፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላ ለአጣሪ ኮሚቴ የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  18. መስሪያ ቤቱ ከተጫራቹ ጋር ከገባው የግዢ ውል አቅርቦት መጠን ላይ በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀር እስከ 20/100 (ሀያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
  19.  ተጫራቾች ስለ ጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡-(0911996314) ወይም ቢሮ ቁጥር 07 በግንባር በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  20. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  21. አሸናፊው ወይም አቅራቢው ድርጅት የአሸነፈበትን እቃ ገቢ ለማድረግ ደረሰኝ ሲያቀርብ የካሽ ሬጅስተር ከአታችመንት ጋር (የእጅ በእጅ ደረሰኝ) ከሆነ ከገቢዎች ደረሰኝ እንዲጠቀሙ የተፈቀደበት ደብዳቤ ማጻፍ አለባቸው ይህ ካልሆነ ግን እቃዎችን ገቢ ማድረግ የማይቻል መሁኑን እናሳውቃለን፡፡
  22. ከጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አቅራቢዎች የድጋፍ ደብዳቤ አጽፈው መምጣት ያለባቸው ከአደራጃቸው የጽ/ቤት የበላይ ኃላፊ ተፈርሞ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ነገር ግን በቡድን መሪ ተፈርሞ የሚመጣ የድጋፍ ደበዳቤ ተቀባይነት የለውም።

ማሳሰቢያ፡-

በጥቃቅንና አነስተኛ : ለተደራጁ : አቅራቢዎች የሚወዳደሩት በሚያመርቱት ምርት (እቃ) ብቻ መሆኑን አውቀው የአምራች (አቅራቢ) የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ይህ ካልሆነ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

ነገር ግን በማያመርቱት ምርት (እቃ) መወዳደር የሚችሉት እንደማንኛውም ተጫራቾች ሲፒኦ) ማቅረብ (ማስያዝ) አለባቸው።

የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ ክፍት ሆኖ የሚቀይበት ጊዜ (አሰር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በመንግስት የስራ ሰዓት በኮሌጁ የባንከ አካውንት 1000002274918 ልደታ ማኒፋከቸሪንግ ኮሌጅ በማስገባት በኮሌጁ ግቢ ግዢ ክፍል በቢሮ ቁጥር 7 መውሰድ ይችላሉ።

የጨረታ ማስከበሪያ በተጫረቱበት ዘርፍ የሞሉትን በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።

ጨረታ ማስከበሪያ ለምሳሌ ቢድቦንድ፣ የባንክ ጋራንቲ፣ በምንም ተቀባይነት እንደማይኖረው እናሳውቃለን።

አድራሻ፡- ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አክሲዮን

 ማህበር ኮካኮላ  ፋብሪካ

ስ.ቁ ፡-

0112736494/0911996314

 የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-09
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው (አስራ አንደኛው) የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-09 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው (አስራ አንደኛው) የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lideta Manufacturing College
  • Buyer address: ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አክሲዮን ማህበር ኮካኮላ ፋብሪካ ገባ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T08:07:54.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders