Food and Beverage
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሀላባ ዞን ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ ለሥራ አገልግሎት እና ለታካሚዎች የሚሆን ንብረቶችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ – መ/ቁ 02/2019
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሀላባ ዞን ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት በጨረታ መለያ ቁጥር ሀ/አጠ/ሆ 03/2019 ለሆስፒታሉ ለሥራ አገልግሎት እና ለታካሚዎች የሚሆን ሎት 1 የመድኃኒት እና የህክምና እቃ ግዥ፣ ሎት 2 ለተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አገልግሎት፣ ሎት 3 የትራስፖርት ጭነት ማመላለስ መኪና የኪራይ አገልግሎት፣ ሎት 4 ህጋዊ ፍቃድ ያለውን ማህበር የጉልበት ስራ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸዉ ድርጅቶች እና ባለንብራቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ በአቅራቢነት ለመሳተፍ የሚያስችል የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ክፍያ ምስክር ወረቀት/TIN number/፣ የቫት ሰርተፊኬት ፤ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የተሰጠ የምስክር ወረቀት ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኋላ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. እያንዳንዳቸው ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000/አስር ሽህ ብር/ ብቻ በባንከ የተረጋገጠ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ /RV/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገፅ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም በማኖር ዋናዉን ሰነድ በአግባቡ በታሸገ ኤንቨሎፕ ዉስጥ በማድረግ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በግልፅ ኤንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ታክስን /VAT/ የሚያካትት መሆን አለበት፡፡ ካልሆነ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
4. የጨረታ ዶክመንት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በመደበኛ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬቶሬት ቢሮ ቁጥር 57 በአካል በመቅረብ የጨረታዉን ሰነድ በስራ ሰዓት ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
5. የጨረታው ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋት በ4፡00 ሰዓት የጨረታዉ ሳጥን የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ ቀን ከጠዋት 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ሳጥን ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
6. አሸናፊ የሆነ አቅራቢ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃዎችን የማስጫኛ አና የማዉረጃ ወጪ እንዲሁም የትራንስፖርት በራሱ ወጪ የሚያቀርብ ይሆናል።
7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046 556 0281/ 0926 182 111 / 0941 985 165 ላይ መደወል ይቻላል።
አድራሻ:- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሀላባ ዞን ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል
የሀላባ ዞን ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-10-15
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋት በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-15 23:00
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋት በ5፡00 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Kulito General Hospital
- Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 27, 2026)
- Posted at: 2026-09-28T12:54:50.000Z
- Source: Qelal Tenders