Transportation Service
የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በከተማው ውስጥ ለሚገኙ አትክልቶች ውሃ የሚያጠጣ ቦቴ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት/ለመከራየት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በከተማው ውስጥ ለሚገኙ አትክልቶች ውሃ የሚያጠጣ ቦቴ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት /ለመከራየት ይፈልጋል።
1. ለተጠየቀው ቦቴ መኪና ኪራይ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax payer registration No) ያላቸው
2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጽ/ቤቱ ስም የሲንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 10545511611211 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት በጽ/ቤቱ የግዢ የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ማንኛውም ተጫራች በሚወዳደርበት ሰነድ ላይ በተሰጠው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ብቻ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ ዋጋውን መሙላት ይኖርበታል።
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የተጠቀሰዉን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ፎቶ ከፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ።
6. ጨረታው የሚከፈተዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ 16ኛዉ ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛዉ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በአዳማ ከተማ ገንዘብ/ፅ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ግዢ ክፍል ዉስጥ ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
7. ማንኛውም ተወዳዳሪ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል።
8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ካሸነፈ ማቅረብ የሚጠበቅበት ሃያ ሶስት /23/ ቦቴዎችን ነው።
9. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበት እያንዳንዱ ቦቴ አስር ሺህ /10000/ ሊትር እና ከዚያ በላይ የሚይዝ መሆን አለበት።
10. ተጫራች ለሚያቀርባቸው ቦቴዎች ቦሎ ያስደረገበትን ማቅረብ አለበት።
11. ተጫራቾች የነዳጅ ዋጋ እና የተለያዩ ጥገናዎችን፣ የሹፌር ወጪን በራሱ ወጪ የሚሸፍን መሆን አለበት።
12. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከመደበኛ የሥራ ቀናት ውጪ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺ ህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። CEAPA
14. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 12-22-58-06 ላይ ማግኘት ይችላሉ።
የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-15
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ 16ኛዉ ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-15 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ 16ኛዉ ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Adama City Finance and Economic Cooperative Bureau
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
- Published on: Addis Zemen (Sep 27, 2026)
- Posted at: 2026-09-28T13:00:06.000Z
- Source: Qelal Tenders