Distribution of Different products

ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) የማይክሮ ኢንሹንስ ሽያጭ ወኪሎችን አሰልጥኖ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የሽያጭ ወኪልነት ሥራ ማስታወቂያ

ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሰረት የማይክሮ ኢንሹንስ ሽያጭ ወኪሎችን አሰልጥኖ ማሰራት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የሥራ ዓይነት

ተፈላጊ መረጃዎችና መስፈርቶች

1

በማይክሮ ኢንሹራንስ ዘርፍ በኮሚሽን ክፍያ የሚሰራ የሽያጭ ወኪል፤

ለድርጅት የማይክሮኢንሹንስ ወኪሎች፡

▪ በንግድ ሕጉ መሠረት እንደ ድርጅት (ካምፓኒ) የተቋቋመ፣

▪ በኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን የተመዘገበ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን፣ ፌዴሬሽን ወይም ሊግ

▪ በተመለከተው የመንግሥት አካል የተመዘገበ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት (NGO)፣

▪ በተመለከተው የመንግሥት አካል የተመዘገበ የዕድር ማኅበር

▪ በተመለከተው የመንግሥት አካል የተመዘገበ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማራ ድርጅት፣

▪ በተመለከተው የመንግሥት አካል የተመዘገበ ማኅበር

▪ በተመለከተው የመንግሥት አካል የተመዘገበ የማኅበራት ዩኒየን

ተጨማሪ መስፈርቶች

• ለድርጅት አመልካች፣ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ዜጎች ወይም በኢትዮጵያ ዝርያ ባላቸው የውጭ ዜጎች ባለቤትነት ሥር መሆን አለበት

▪ የሚመለከተው ሰው(Responsible Person) መስየም አለበት፤ ይህ ሰውም፦ በብሔራዊ ባንክ የማይክሮኢንሹንስ ሽያጭ ወኪሎች አዋጅ ቁጥር SM|B/4/2026 በአንቀጽ 7 መሠረት ተገቢውን ሥልጠና መስፈርቶችን ማሟላት አለበት

▪ በማጭበርበር ወይም በታማኝነት ጉድለት ወንጀል በፍርድ ቤት ያልተፈረደበት መሆን አለበት

▪ የሙያ ኃላፊነት መድን (Professional Indernity) መያዝ አለበት፤ ቢያንስ ከመጨረሻው የሂሳብ ዓመት ከተገኘው ዓመታዊ ኮሚሽን

የ10%፣ ወይም ብር 40,000 (አርባ ሺህ)፡፡

▪ በቅድሚያ የሥልጠናና አገልግሎት ስምምነት ለመፈረም ፈቃደኛ የሆነ፣

▪ በቅድሚያ ለፈቃድ ማውጫ እና ለሰነድ ማስመርመሪያ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) መክፈል የሚችሉ፣

ለግለሰብ የማይክሮ ኢንሹንስ ወኪል አመልካቾ፡

▪ የኢትዮጵያ ዜጋ ወይም የኢትዮጵያ ዝርያ ያለው የውጭ ዜጋ መሆን አለበት

▪ ቢያንስ የ12ኛ ክፍል አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ ማጠናቀቅ አለበት

▪ በብሔራዊ ባንክ የማይክሮኢንሹንስ ሽያጭ ወኪሎች አዋጅ ቁጥር SM/B/4/2026 አንቀጽ 7 መሠረት ተገቢውን ሥልጠና መስፈርቶችን ማሟላት አለበት

▪ በማጭበርበር ወይም በታማኝነት ጉድለት ወንጀል በፍርድ ቤት ያልተፈረደበት መሆን አለበት

• ለእያንዳንዱ የተፈቀደለት የምርት ምድብ ቢያንስ ብር 10,000 (አሥር ሺህ) የሙያ ኃላፊነት መድን መያዝ አለበት

▪ በቅድሚያ የሥልጠናና አገልግሎት ስምምነት ለመፈረም ፈቃደኛ የሆነ፣

▪ በቅድሚያ ለፈቃድ ማውጫ እና ለሰነድ ማስመርመሪያ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) መክፈል የሚችሉ፣

ማሳሰቢያ፡-

ከላይ የተጠቀሱትን ተፈላጊ መረጃዎችን እና መስፈርቶችን የሚያሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ውሰጥ ቅዳሜ ጠዋትን ጨምሮ ዘውትር በስራ ሰዓት የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃችሁን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ በንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) ዋና መ/ቤት ቦሌ ደንበል ሲቲ ሴንተር 7ኛ ፎቅ በሪሰርችና ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት መምሪያ በአካል በመቅረብ ማመልከት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-54 37 05 መደወል ይችላሉ።


Tender details

  • Deadline: 2026-10-08
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-10-08 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰኣት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Nib Insurance Company S.C.
  • Buyer TIN: 0000211714
  • Published on: Reporter (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T15:12:00.000Z
  • Buyer website: https://www.nibinsurancethiopia.com/
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders