Land Lease & Real Estate
የደብረ ማርቆስ ከ/አስ/መ/መምሪያ ለመኖሪያ እና ንግድ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል
Description
የሊዝ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደማ/01/2019
የጨረታ ዙር 1ኛ፤የጨረታ ዓይነት መደበኛ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መሬት ቢሮ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004፣ አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ”ሀ” እስከ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያ እና ንግድ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ትችላላችሁ።
- ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል ከአገልግሎት አቅርቦት ተጠሪ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን። በ10ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው እስከ ቀኑ 10፡00 ብቻ ይሆናል።
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል።
- የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸገው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ኛው ቀን 11፡00 ነው።
- ቦታውን መጎብኘት ለምትፈልጉ ተጫራቾች የጉብኝት ፕሮግራም በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 በመምሪያው ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤ 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ዉጤት ከሀያ በመቶ ያላነሰ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት ሰነድ ከዋጋ እና የሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚደረገው የጨረታው አሸናፊ ከተረጋገጠበት ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደብረ ማርቆስ ከ/አስ/መ/መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-10-07
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸገው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-08 09:00
- Bid opening (note): ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Be'kur (Sep 28, 2026)
- Posted at: 2026-09-29T08:05:50.000Z
- Source: Qelal Tenders