Building Construction
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/በኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለኮንታ ኮይሻ ወረዳ አስ/ር ጽ/ቤት በኮይሻ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድንገተኛ መታከሚያ አንድ ብሎክ ህንፃ ግንባታ በ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመገንባት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/በኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለኮንታ ኮይሻ ወረዳ አስ/ር ጽ/ቤት በኮይሻ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድንገተኛ መታከሚያ አንድ ብሎክ ህንፃ ግንባታ በ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመገንባት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ለመጫረት የምትፈልጉ፡-
1/ በግንባታው ዘርፍ ደረጃ አምስት (BC-5/GC5) እና ከዚያ በላይ የተመዘገበ፣
2/ የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣
3/ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
4/ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና በዘመኑ የታደሰ የግንባታ ስራ ፍቃድ፣
5/ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት፣
6/ የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ከግብር ዕዳ ነፃ የሚል ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል፣
7/ በመንግስት ግዥ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣
8/ የመልካም ስራ አፈፃፀም የ2015፣ የ2016፣ የ2017፣የ2018 ዓ/ም ውስጥ ሶስት እና ከዛ በላይ ማቅረብ የሚችል፤
9/ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር ብቻ በCPO ከታወቀ ባንክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
10/ ተጫራቾች የጨረታ ዶክምንት የማይመለስ 1,000 (አንድ ሺህ) ብር ብቻ በመክፍል ከኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር G+003 መውሰድ ይኖርባቸዋል፣
11/ ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ እስከ 21ኛው ቀን ድረስ በኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመቅረብ የጨረታ ዶክመንት በመግዛትና በዋጋ ማቅረብያ በመሙላት ቴክኒካል ኦርጅናል 1፣ ቴክኒካል ኮፒ 1፣ ፋይናንሻል ኦርጅናል 1፣ እና ፋይናንሻል ኮፒ 2 በድምሩ 5 ፖስታ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ በኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
12/ የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው ከላይ በተባለው 21ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት በኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ይከፈታል።
13/ በጨረታ ማስታወቂያ ያልተገለፁ ሌሎች የመወዳደርያ ነጥቦች (መስፈርቶች) በጨረታ ዶክመንቱ ላይ በጥንቃቄ ተግባራዊ ይደረጋል፣
14/ በጨረታ ማስታወቂያ እና ዶክመንቱ ላይ የተገለፁትን የመወዳደርያ ነጥቦቹን ያሟሉ ተጫራቾች ብቻ ቴክኒካል ግምገማ ያልፋሉ፣
15/ ተጫራቾች በጨረታ ዶክመንቱ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ሃሳቦች ከተገኙ የጨረታ መክፈቻ ቀን ከመድረሱ ሦስት ቀናት አስቀድሞ በአካል ወይም ከታች በተመለከተው ስልክ በመደወል ማስመዝገብ ይጠበቅበታል።
16/ 5% ወደ ላይ እና ወደ ታች የአርትመቲክ ስህተት ተግባራዊ/ውድቅ ይደረጋል።
17/ መስርያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፦
በስልክ ቁጥር 0910692839/0917007585
አድራሻ፡- በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ ኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከጅማ ከተማ በስተደቡብ 166 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በኮይሻ ከተማ ይገኛል።
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/በኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-20
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-20 14:30
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: SNNPRS Konta Koysha Woreda FEDB
- Bid bond: 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር
- Bid document price: 1,000 (አንድ ሺህ) ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 30, 2026)
- Posted at: 2026-09-30T11:21:55.000Z
- Source: Qelal Tenders