Hand Tools and Workshop Equipment
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የመበየጃ ኤሌክትሮድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/01/2019
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የመበየጃ ኤሌክትሮድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የ2018/2019 ዓ/ም የተጨማሪእሴትታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት የታክስ ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ገርጂ የቀድሞው ኤምፔሪያል ህንፃ ከሚገኘው የፋብሪካው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው በዕለቱ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
Tender details
- Deadline: 2026-10-20
- Bid closing time: 09:30
- Bid opening: 2026-10-20 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Mugher Cement Factory
- Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
- Bid bond: 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 575.00 (አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 01, 2026)
- Posted at: 2026-10-01T07:18:50.000Z
- Source: Qelal Tenders