Pharmaceutical Products

በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል ለህብረተሰብ ፋርማሲ እና ለኢትዮጵያ ፋርማሲ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ህጋዊና ብቁ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ድ / ዳ / ድ / መ/ሆ/02/19

በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል ለህብረተሰብ ፋርማሲ እና ለኢትዮጵያ ፋርማሲ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም መድሃኒቶችና ሰፕላይ እና ሪኤጀንቶች ፣ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ፣ የምግብ እቃዎች ፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች ፣ የህትመት ስራዎች ፣ ጨርቃ ጨርቆች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች ፣ አናፂ እቃዎች እና የመኪና ጎማዎችና ባትሪዎች በግልጽ ጨረታ ህጋዊና ብቁ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ለ2019 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ ግብር የከፈሉበት እንዲሁም እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል

3. ለመድሃኒት ከ EFDA የታደሰ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል

4. በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

5. ተጫራቾች የታክስ መለያ ቁጥር (TIN No.) ያላቸውና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል በድል ጮራ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር A/2 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

7. መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም (CPO) ከጨረታው ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. የጨረታ ሰነዱ የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን ጠዋት 3:30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ግዥ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር A/2 ይከፈታል።

10. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለጸለት አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ 10% ከሆስፒታሉ ጋር ውል መፈረም አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በጨረታው አሸናፊነቱን ለመሰረዝ ከጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

11. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ፣ ሙሉ አድራሻቸውን እና ፊርማቸውን እንዲሁም የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

12. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል

ስልክ ቁጥር 025 211 5693 / 0982 540 408 / 0901 103 211 /

ፖስታ ሳጥን ቁጥር 177

በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-10-19
  • Bid closing time: 15:30
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን ጠዋት 3:30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-19 10:00
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Dire Dawa Dil Chora Hospital
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 1,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Oct 01, 2026)
  • Posted at: 2026-10-01T07:29:29.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders