Installation, Maintenance and Other Engineering Services

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት (አዲስ አባባ) ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የአቅርቦት እና ገጠማ ሥራዎች ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥሮች DCE/SF/133/2026 እና DCE/SF/134/2026

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት (አዲስ አባባ) ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሠንጠረዥ በዝርዝር የተጠቀሱትን የተለያዩ የአቅርቦት እና ገጠማ ሥራዎች ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የዕቃውን አይነት

የፕሮጀክት ስም

የጨረታ ቁጥር

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ማስከበሪያ

1

Supply & fix Elevator

ለፈደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት

DCE/SF/133/2026

ጥቅምት 04/2019 ዓ.ም 4፡15 ሰዓት

ጥቅምት 04/2019 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት

100,000.00

2

Supply and fix Submersible Pump

ፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን

DCE/SF/134/2026

ጥቅምት 04/2019 8:15 ሰዓት

ጥቅምት 04/2019 ዓ.ም 8:30 ሰዓት

100,000.00

ስለሆነም፡-

1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ፣ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ...ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ (Bid Bond) 120 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ለያንዳንዱ ጨረታ ቁጥር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡የመድን ድርጅቶች ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለያንዳንዱ ጨረታ ቁጥር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት አዲሱ ቢሮ ቃሊቲ ቶታል ማድያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ ውስጥ

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0911 171 751 / 0913 297 297

E-mail አድራሻ [email protected]

የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com

ቃሊቲ ቶታል ማድያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-14
  • Bid closing time: 14:15
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-10-14 14:30
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
  • Buyer address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
  • Bid bond: 100,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 01, 2026)
  • Posted at: 2026-10-01T07:45:42.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders