Building Construction
በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ለሚያስገነባቸው የሠራዊቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የማጠናቀቂያ ስራ ግንባታ ሲቪል ስራዎች /Civil Work/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር መሰፋ/ብ/ግ/ጨ/03/2019
በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ለሚያስገነባቸው የሠራዊቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የማጠናቀቂያ ስራ ግንባታ ሲቪል ስራዎች /Civil Work / በግንባታው ዘርፍ GC/BC ደረጃ 1 - 4 ከዚህ በታች የተገለፀውን ሲቪል ስራዎች/Civil work/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ጋሻ ፕሮጀክት .....የማጠናቀቂያ ስራ /Civile work/....
በዚህም መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው የምትሳተፉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ/ VAT Registration Certificate/፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡ እና የቲን ሰርተፊኬት የብቃት ሰርተፊኬት tax clearance certificate የመንግሰት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መ.ሰ.ፋ. ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 15 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማለትም ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር ብቻ/በባንክ በተመሰከረለት/ሲ.ፒ.ኦ/ ባንክ ጋራንቲ ብቻ በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ስም ከጨረታው ኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ሰነዶቻቸውን ኦሪጂናል እና አንድ አንድ ኮፒ ለየብቻ ለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 15 በመምጣት መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። እንዲሁም ተያያዥ ዶክመንቶች ማቅረብ አለባቸው።
5. ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ልክ 8፡00 ሰአት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 መ.ሰ.ፋ ግዥ ክፍል ይከፈታል።
6. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው እና የውል ስምምነት የሚፈፅሙ ይሆናል።
7. በጨረታ ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
8. ፋውንዴሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስዳው መንገድ ላንድ ማርክ ሆስፒታል አጠገብ
ስልክ ቁጥር 011 557 5227 / 09 10 99 38 14
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን
Tender details
- Deadline: 2026-10-17
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ልክ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-17 14:30
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defense Force Foundation
- Buyer address: ከደንበል ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ ናዝራ ሆቴል ፊት ለፊት ጫካ ቡና አጠገብ
- Bid bond: 200,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 02, 2026)
- Posted at: 2026-10-02T07:11:27.000Z
- Source: Qelal Tenders