Promotional Items

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለድርጅቱ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

CN/NCB/7/19

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለድርጅታችን የሚያስፈልጉ

  • ሎት1፡- የፕሮሞሽን ዕቃዎች (Promotional Items & Merchandise)፡- Leather Calendar, Desk Calendar, T- Shirt, Warless Mouse
  • ሎት2፡- የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች (Different Furniture)
  • ሎት3:- የእሳት ማጥፊያ (Fire Extinguisher & Office Equipment)□- Notice board, White board Suggestion box, Giant stapler ማቅረብ የሚችሉ

ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ኢንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እና ከሠዓት 7፡00-11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት 2፡00-6፡00) ማግኘት ይቻላል:: የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ለሎት 1 እና ሎት 2 ብር 100,000 ለሎት 3 ብር 50,000 ለእያንዳንዳቸው በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል።

ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ:: ጨረታው በዚሁ ዕለት ጠዋት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: የዕቃዎች ርክክብ የሚደረግበት ቦታ ገርጂ የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ይሆናል:: ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል።

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው

የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር 0111 569 992

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-13
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-13 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Commercial Nominees P.L.C.
  • Buyer TIN: 0000958158
  • Buyer address: ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 03, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T08:11:55.000Z
  • Buyer website: https://commercialnominees.com/
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders