Hand Tools and Workshop Equipment
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ. አሰላ ብቅል ፋብሪካ የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ በመጋበዝ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ፡-
- LOT: 1. Workshop Materials፡- NCB/OACFLTD/AMF/01/2019
- LOT: 2. Electrical Materials፦ NCB/OACFLTD/AMF/02/2019)
- LOT: 3. Bearing, Mechanical Seal and Oil Seal and V-Belt፦NCB/OACFLTD/AMF/03/2019
- LOT: 4. Mechanical and Electrical Tools፦ NCB/OACFLTD/AMF/04/2019 ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በመጋበዝ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
1. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በፋብሪካችን አካውንት በኢትዮጰያ ንግድ ባንክ 1000257808697 ወይም በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1000043405229 በመክፈል ገቢ በማድረግ። ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት 2፡00-6፡00 ከሰዓት በኃላ 7፡00-10፡00 ሰዓት ድረስ ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወሰደው መንገድ ላይ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ወይም ኣሰላ-ቁሉምሳ ከሚገኘው ፋብሪካችን ቢሮ ቁጥር 003 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በፖስታ በማሸግ አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና መ/ቤት በኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከታች ከተጠቀሰው የመዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለLOT፡ 1 ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለLOT: 2 ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለLOT:3 ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) እና ለLOT:4 ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ለየብቻ በማስያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን፡- ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን LOT 1 እና LOT 2 ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ፤ LOT 3 እና LOT4 ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 6፡00 ሰዓት ላይ ለመግኘት በሚሹ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና መ/ቤት የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ ሰባተኛ ፎቆ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። የመከፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
6. ፋብሪካው በዚህ ጨረታ ሰነድ ከተገለጸው ብዛት 20% (ሃያ በመቶ) በመቀነስ ወይም 30% (ሰላሳ በመቶ) በመጨመር በተመላሳይ ዋጋ መግዛት ይችላል።
7. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ተጫራቾች በጨረታ ማስታወቂያና በተጫራቾች መመሪያ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነጥብ ካለና ተጨማሪ
ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 09 65 65 04 81/ 09 65 65 02 85 በሥራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት
ፌዴሬሽን ኃላ.የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ
Tender details
- Deadline: 2026-10-24
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታው ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-10-24 12:00
- Bid opening (note): የጨረታው ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Oromia
- Publishing entity: Assela Malt Factory
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 03, 2026)
- Posted at: 2026-10-05T08:27:52.000Z
- Source: Qelal Tenders