Construction Machinery and Equipment

የዲላ ትምህርት ኮሌጅ ቆርቆሮ 32 ጌጅ፣ LTZ 1.5 ባለ 48፣ መስታወት ባለ 6mm፣ ፑቲ፣ ሚስማር፣ ሲሚንቶ፣ የብረት ቀለም፣ አንቲረስት እና ተመሳሳይ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2019

የዲላ ትምህርት ኮሌጅ 

ሀ, ለህንጻ ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚዎች ዕድሳትና ጥገና ማለትም

1 ቆርቆሮ 32 ጌጅ፣ LTZ 1.5 ባለ 48፣ መስታወት ባለ 6mm ፣ ፑቲ፣ ሚስማር፣ ሲሚንቶ፣ የብረት ቀለም፣ አንቲረስት፣ እና ተመሳሳይ ዕቃዎችን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10000.00 በማስያዝ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት ከላይ የተጠቀሱ እቃዎችን ዋጋ ቫትን አካቶ በመሙላት ኮሌጁ ለዚሁ ሥራ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ለ. በዚሁ መሰረት

1. በጨረታው የሚሣተፋ ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር አጠናቅቀው የከፈሉ፣ የምዝገባ የምሰክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች በ(VAT) ከፋይነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፣

3. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው እራሣቸውን ማግለል አይችሉም፣

4. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸውየሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፣

5. ተጫራቾች በጨረታው ለሚሣተፋባቸው ዕቃዎች ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ከላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች በጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ፣

7. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

8. ኮሌጁ በጨረታው አሸናፊ ለሆነው ድርጅት ክፍያ የሚፈጽመው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው ፣

9. ተጫራቹ ለጨረታው የሚያቀርቧቸውን ሠነዶች ዋናውንና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የዲላ ትምህርት ኮሌጅ የግልጽ ጨረታ ቁጥር 02/2019 ዓ/ም በማለት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል። ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመሥሪያ ቤቱ የማኔጅመንት መሰብሰቢያ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል።

11. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት በጨረታው ያሸነፈባቸውን እቃዎች ማንኛውም ወጪ የጉምሩክ ቀረጥን ጨምሮ በመሸፈን ዕቃዎቹን የሚያስረክበው ዲላ ትም/ ኮሌጅ ነው።

12.ተጫራቾች ለጨረታ በሠነድ ላይ ያቀረቡት ዋጋ ላሸነፋባቸው ቋሚና አላቂ ዕቃዎች እስከሚያስረክቡበት ጊዜ ድረስ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።

13. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% በማስያዝ ከመሥሪያ ቤቱ ጋር የሽያጭ እና የግዥ ውል ይፈራረማሉ።

14. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ የዕቃዎቹን አይነት፣ የአምራቹን ስም፣ የተመረተበትን ሀገር፣ የሞዴል ቁጥርና የተመረተበትን ዓመት ጭምር ማካተት ይኖርበታል። የስፔስፊኬሽን መግለጫ የሚያስፈልጋቸው እቃዎች በአይነት በፎቶና የአቅም መለያ እንደአማራጭ ይቅረብ።

15. ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፣

16. የዕቃው ርክክብ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር የሚከናወነው የግዥው መሥሪያ ቤት ባለሙያዎች በሚያደርጉት የጥራትም ሆነ የዓይነት ምርመራ በ /Specification/ መሠረት ትክክለኛነቱ ሲረጋገጥ ይሆናል፣

17. የጨረታ ሰነዱን በዲላ ትምህርት ኮሌጅ አካውንት ቁጥር 1000200244382 ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር በግዥ ማግኘት ይችላሉ።

18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ እንዲሁም ብዛት የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።

የዲላ ትምህርት ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-19
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-19 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Dilla Education College
  • Bid bond: 10000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Oct 04, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T10:56:06.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders