Products and Services
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የተለያዩ የቁም ደን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር OFWE/GU- 03/2019 ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ቦራና ጉጅ ቅ/ጽ/ቤት እና ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ፤ እንዲሁም ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ላይ የፈረንጅ ጥድ እና የ Gravelea roubsta" ድብልቅ ግንድላ እና የፈረንጅ ጥድ እና የባህር ዛፍ ድብልቅ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት ቦሬ ድስትሪክት፤ ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ምዕራብ ወለጋ ድስትርክት፤ ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጃሎ ሙክታር ዲስትሪክት እና አርሲ ቅ/ጽ/ቤት አዳባ ዶዶላ ዲስትሪክት ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
1. የግንዲላ እና የእንጨት መሰንጠቂያ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የቫት (VAT) ተመዝጋቢና “TN number” ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል/ ኦይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 እና ጨረታው በወጣበት ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ጊምቢ ከተማ፤ ሀራርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጭሮ ከተማ፤ ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት መቱ ከተማ፤ ቦራና ጉጅ ቅ/ጽ/ቤት አዶላ ከተማ፤ እና አርሲ ቅ/ጽ/ቤት ነጌሌ አርሲ ከተማ በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ።
2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታተይ ቀናት ይቆይል።
3. ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የምትጫረቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች፤ በቅ/ጽ/ቤት የምትጫረቱ መ/ቤቱ ከሚገኝበት ከተማ በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO)ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
5. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 124 0249 በመደወል መጠየቅ ወይም “ www.oromiaforest.et ድህረ-ገፅ መጎብኘት ይችላሉ።
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-10-17
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታተይ ቀናት ይቆይል
- Bid opening: 2026-10-17 17:00
- Bid opening (note): ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Forest and Wildlife Enterprise
- Buyer address: አዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቀበና ኦይል ሊቢያ አጠገብ
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዳቸው
- Published on: Addis Zemen (Oct 03, 2026)
- Posted at: 2026-10-05T11:27:35.000Z
- Buyer website: https://www.oromiaforest.gov.et
- Source: Qelal Tenders