Construction Machinery

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል በጅማ ዞን የጉማይ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ለመንገድ ሥራ የሚውል ማሽኖችን መከራየት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2019

ከላይ በርእሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል በጅማ ዞን የጉማይ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ለመንግስት መስሪያ ቤት ለገጠር መንገድ በ2019 E.C. የበጀት ዓመት የመንግድ ሥራ ማሽኖችን በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት አወዳድሮ ለመንገድ ሥራ የሚውል ማሽኖችን መከራየት ይፈልጋል። 

ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው መስፈርቶች -

1ኛ የመንገድ ንግድ ማሽን ክራይ ፍቃድ ያላቸው እና የ2018 ዓ.ም ግብር የከፈሉ

2ኛ, በዘርፉ የ2019ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው

3ኛ. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው፣

4ኛ. የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያለው።

5ኛ. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

6ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከ አጠቃላይ ዋጋ የነዳጅ ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO (ቼክ) (unconditional bank guarantee) ማስያዝ የሚችል።

7ኛ. የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 1000/ አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከጉ/ወ/ ገንዘብ /ጽ/ቤት መግዛት የሚችል።

8ኛ. ተወዳዳሪዎች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተካታታይ ቀናት ( ቅዳሜ ና እሁድን ሳይጨምር) የጨረታ ሰነዱን ገዝቶ ማስገባት የሚችል፤

9ኛ. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻውን እና የድርጅቱን ስም እና ማህተም በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሃያአንደኛው (21) ቀን 6:00 ሰዓት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10ኛ. ጨረታው በተባለበት ቀን እና ሰዓት ገብቶ ካለቀ በኃላ በእለቱ 6:30 (ስድስት ሰዓት ተኩል) ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8:00 (ስምንት ሰዓት) በጉ/ወ/ገ/ጽ/ ቤት ይከፈታል።

11ኛ. አሸናፊ ተጫራቾች ከጽሕፈት ቤቱ ጋር ውል መፈራረም የሚችሉ እና የውል ማስከበሪያ/ ዋስትና ያሸነፈበትን ዋጋ 10% በቼክ ማስያዝ የሚችሉ መሆን እንዳለባቸው።

12ኛ. እዚህ ማስታወቂያ ላይ ያልተጠቀሱ መስፈርቶችን ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ ተካተዋል

ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 259 17 110 586/ 09 17 01 68 06 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል በጅማ ዞን የጉማይ ወረዳ ገንዘብ / ጽ / ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-26
  • Bid closing time: 12:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሃያአንደኛው (21) ቀን 6:30
  • Bid opening: 2026-10-26 14:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሃያአንደኛው (21) ቀን 8:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Oromia National Regional Government, Jimma Zone, Gumay District Finance Office
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 05, 2026)
  • Posted at: 2026-10-06T07:49:58.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders