Food Items and Drinks
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (onboard passenger service) እና ለስካይላይት ሆቴል አገልግሎት የሚውል የተጣራ ማር ከሚያመርቱ ድርጅቶች ጋር በኮንትራት ስምምነት ለሦስት (3) ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመስራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- SSNT-T648
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (onboard passenger service) እና ለስካይላይት ሆቴል አገልግሎት የሚውል የተጣራ ማር ከሚያመርቱ ድርጅቶች ጋር በኮንትራት ስምምነት ለሦስት (3) ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመስራት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-
በአገልግሎቱ ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፤ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ምዝገባ ወረቀት ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ ፣ አንድ (1) ዓመትና እና ከዛ በላይ የስራ ልምድ ያለው ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ሁለት መቶ ብር (ብር 200.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T648 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሶስት መቶ ሺህ ብር (300,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቋም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኘው የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን በ 9:00 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ -
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር፡ 011-517-4552
ወ/ሮ ብርቱኳን ሰሙ
ኢ-ሜይል: [email protected]
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-11-06
- Bid closing time: 14:30
- Bid opening: 2026-11-06 15:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
- Buyer TIN: 0000028498
- Bid bond: 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 05, 2026)
- Posted at: 2026-10-06T08:44:26.000Z
- Source: Qelal Tenders